በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአቅርቦት እጥረት ምክኒያት አይደር ሆስፒታል ሥራ ማቋረጡን አስታወቀ


በአቅርቦት እጥረት ምክኒያት አይደር ሆስፒታል ሥራ ማቋረጡን አስታወቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:09 0:00

በአቅርቦት እጥረት ምክኒያት አይደር ሆስፒታል ሥራ ማቋረጡን አስታወቀ

በትግራይ ክልል ትልቁ የጤና ተቋም አይደር ሪፈራል ሆስፒታል ከትናንት ማታ ጀምሮ ሥራ ማቋረጡን ገለፀ። ሆስፒታሉ በሕክምና መሳሪያዎች፣ መድኃኒት እና ነዳጅ እጦት ምክኒያት ሥራውን ማቆሙ አስታውቋል።

የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶ/ር ክብሮም ገብረስላሴ፤ ሆስፒታሉ በድንገተኛ ሕክምና ለሚመጡ የተወሰኑ ታካሚዎች ካልሆነ በስተቀር ምንም ዓይነት አገልግሎት እንደማይሰጡ ተናግረዋል።

በሌላ በኩል ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ጋር በመተባበር በሀገሪቱ ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች ልዩ ልዩ ድጋፎች ማድረጋቸውን ባለፈው ሳምንት ማጠናቀቂያ ለአሜሪካ ድምፅ ገልጾ ነበር።

ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ኢትዮጵያ ውስጥ ግጭት በተከሰተባቸው አካባቢዎች ልዩ ልዩ ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ የገለፁት የኮሚቴው የኢትዮጵያ ቅርንጫፍ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፓትሪክ መጌቫንድ ባለፈው ሳምንት በ5ኛ ዙር በተላከ ድጋፍ መድሃኒት፣ ምግብና ቁሳቁሶች የጫኑ የእርዳታ ተሽከርካሪዎች ትግራይ መግባታቸውን ገልፀው ነበር።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያዳምጡ።

XS
SM
MD
LG