በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዘለንስኪ አማካሪ ሩሲያ በድርድር አትታመንም ጦርነቱ የሚቆመው በኃይል ብቻ ነው አሉ


የፕሬዚዳንት ዘለንስኪ አማካሪና የዩክሬን ተደራዳሪ ሚክሃይሎ ፖዶልያክ በኢንስታቡል ቱርክ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሲሰጡ እኤአ መጋቢት 29/2022
የፕሬዚዳንት ዘለንስኪ አማካሪና የዩክሬን ተደራዳሪ ሚክሃይሎ ፖዶልያክ በኢንስታቡል ቱርክ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሲሰጡ እኤአ መጋቢት 29/2022

የዩክሬን ፕሬዚዳንት አማካሪና ዋነኛው የሰላም ተደራዳሪ ሚካሃይሎ ፖዶልያክ "ከሩሲያ ጋር የሚደረግ ማናቸውም ስምምነት ተአማኒ አይደለም ሞስኮ ወረራዋን የምታቆመው በኃይል ብቻ ነው" ሲሉ ተናገሩ፡፡

አማካሪው ዛሬ በቴሌግራም ባስተላለፉት መልዕክታቸው "ከሩሲያ ጋር የሚደረግ ስምምነት የሽራፊ ሳንቲም ያህል እንኳ ዋጋ አያወጣም፡፡" በማለት "ሁሉ ጊዜ በክፋትና በፕሮጋንዳ ከሚዋሽ አካል ጋር መደራደር ይቻላል?" ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

ሩሲያና ዩክሬን እርስ በርስ የሚወነጃጀሉ በመሆናቸው በመካከላቸው የሚደረግ የፊት ለፊት የሰላም ንግግር እኤአ ከመጋቢት 29 ወዲህ መቆሙ ተነግሯል፡፡

ባላፈው ሰኞ ፕሬዚዳንት ዘለንስኪ መነጋገር የሚፈልጉት በቀጥታ ከሩሲያው መሪ ቭላድሚ ፑቲን ጋር ብቻ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

ክሬምሊን ባላፈው ዓርብ ባወጣው መግለጫ ደግሞ፣ በሁለቱ አገሮች መካከል ያለው ንግግር መቆሙን ገልጾ ምክንያቱም ”ዩክሬን ምን እንደምትፈልግ ግልጽ አይደለም” ማለቱን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

የክሬምሊን ቃል አቀባይ "የዩክሬን ባለሥልጣናት ሁሌም የሚሰጡት መግለጫ እርስ በርሱ የተምታታ ነው" ብለዋል፡፡

XS
SM
MD
LG