በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባይደን ለባህር ኃይል አካዳሚ ምሩቃን ስለ ሩሲያና ቻይና ተናገሩ


የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በባህር ኃይል አካዳሚ ምሩቃን ስነስርዓት ላይ ዕኤአ ግንቦት 27/2022
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በባህር ኃይል አካዳሚ ምሩቃን ስነስርዓት ላይ ዕኤአ ግንቦት 27/2022

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ነጻው ማህበረሰብ ከሩሲያና ከቻይና አደጋ የተደቀነበት በመሆኑ “እናንተ የዲፕሎማሲ ተከላካይና ወኪሎች ናችሁ” ሲሉ ትናንት ዓርብ ለተመረቁት የባህር ኃይል አባላት ተናገሩ፡፡

ሜሪላንድ አናፖልስ በሚገኘው የባህር ኃይል አካዳሚ ተገኝተው 1ሺ ለሚደርሱ ምሩቃን ንግግር ያሰሙት ባይደን የሩሲያን ወረራና የቻይናን የባህር ላይ መስፋፋት አንስተዋል፡፡

“ዓለም በመልክአ ምድር (ጂኦግራፊ) ብቻ ሳይሆን፣ በጋራ እሴቶችም የሚተባበር መሆኑን በሩሲያው ወረራ አሳይቷል” ያሉት ባይደን፣ እናንተም “የአውሮፓና የኢንዶ ፓስፊክ አጋሮቻችንን ታግዛላችሁ” ብለዋል፡፡

የቻይና ደቡባዊ ባህርና ከዚያም ባሻገር ያሉትን ዓለም አቀፍ የባህር ላይ መስመሮች ወይም የመጓጓዣ መንገዶች ፣ ለዓለም አቀፉ ስርዐት መከበርም ሆነ ምጣኔ ሀብት ቁልፍ በመሆናቸው እነሱን መጠበቅ ኃላፊነታቸው መሆኑንም ባይደን ለምሩቃኑ ገልጸዋል፡፡

ባይደን በዛሬው እለትም በደለዌር ዩኒቨርስቲ በሚካሄደው የተማሪዎች ምርቃት ስነ ስር ዓት ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡

ፕሬዘዳንቱ 19 ህጻናት በተገደሉበት የቴክሳሱ የትምህር ቤት ጥቃት፣ ልጆቻቸው የሞቱባቸውን ወላጆች ለማነጋገር ነገ እሁድ ወደ ዩቫልዲ እንደሚያቀኑም ተነግሯል፡፡

XS
SM
MD
LG