በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአሜሪካ ትልቁ የመሳሪያ ማህበር ጉባኤውን በቴክሳስ አካሄደ


በመሳሪያ ማህበሩ ዓመታዊ ጉባኤና የመሳሪያ ሽያጭ ትርኢት ከሚካሄድበት ስፍራ ተገኝተው፣ መሳሪያ ለመግዛት የተሰለፉ አሜሪካውያን ቴክሳስ ሂውስተን እኤአ ግንቦት 26/ 2022
በመሳሪያ ማህበሩ ዓመታዊ ጉባኤና የመሳሪያ ሽያጭ ትርኢት ከሚካሄድበት ስፍራ ተገኝተው፣ መሳሪያ ለመግዛት የተሰለፉ አሜሪካውያን ቴክሳስ ሂውስተን እኤአ ግንቦት 26/ 2022

በአሜሪካ ትልቁ የመሳሪያ ሽያጭ ጠበቃና ተሟጋች የሆነው ብሄራዊ የመሳሪያ ማህበር ትናንት ቴክሳስ ውስጥ ዓመታዊ ጉባኤውን አካሂዷል፡፡

19 ህጻናት ከተገደሉበት የቴክሳሱ ዩቫልዲ ትምህር ቤት 500 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በሚገኝ ስፍራ በተካሄደው ጉባኤና የመሳሪያ ሽያጭ ትርኢት ላይ ለመካፈል ከ50ሺ በላይ የማህበሩ አባላት መመዝገባቸውን ማህበሩ አስታውቋል፡፡

ዝግጅቱን ለሌላ ጊዜ እንዲያስተላልፈው ተጠይቆ የነበረው ብሄራዊ የመሳሪያዎች ማህበር ሥራ አስፈጻሚ ዊይን ላፒየር እያንዳንዱ የማህበሩ አባል በጉዳዩ ማዘኑን ገልጸዋል፡፡

“እኛ ከዚህ ማህበረሰብና ከመላው አሜሪካውያን ጋር በጸሎት እንገኛለን፣ እኛም ወንድ ልጆች ሴት ልጆችና የምናወዳቸው ልጆች አሉን፡፡ ይህ አሳዛኝ ድርጊት አሁን ብዙዎች እያለፉበት እንዳለው አንጀት የሚነካ የማይገመት ህመም የሚፈጥር ነገር ነው” ብለዋል፡፡

ግድያውን ተከትሎ ፕሬዘዳንት ባይደን ባሰሙት ንግግር “መሳሪያ ሻጮች ሁለት አስርት ዓመታት ሙሉ ትልቁን ትርፍ የሚያጋብሱበትን የማጥቂያ መሳሪያዎችን ሲያሻሽጡ ኖረዋል ይህን ኢንደስትሪ ማቆም የምንችልበት አቅም ሊኖረን ይገባል” በማለት የመሳሪያ ህግ በአስቸኳይ እንዲወጣ ጠይቀዋል፡፡

በመሳሪያ ማህበሩ ጉባኤ ላይ ንግግራቸው የተሰማው የቀደሞ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ “ይህ ዓይነቱ ንግግር ከፋፋይና አደገኛ ነው ከሁሉም በላይ ደግሞ ስህተት ነው በፖለቲካችን ውስጥ ስፍራ አይኖረውም” ብለዋል፡፡

ትራምፕ አያይዘውም “ እንደሁልጊዜውም እንዲህ አሳዛኝ ነገር በተከሰተ ማግስት በግራ ፖለቲከኞች የመሳሪያ ቁጥጥር ፖሊሲ ይደረጋል፣ እስካሁን በግራው ግፊት የወጡ ፖሊሲዎች አሰቃቂውን ነገር እንዳይደርስ በተከላከሉ ነበር" በማለት ተናግረዋል፡፡

የሂውስተን ከተማ የሰላምና ፍትህ ማዕከል ፕሬዚዳንት ቢል ክሮሲየር በሰጡት አስተያየት

“ከተማችንን ለእነዚህ ለመሳሪያ አምራቾችና ለኛ ለመራጮች ሳይሆን ለነሱ ለቆሙ ፖለቲከኞች ክፍት በማድረጋችን የተሰደብኩ ያህል ይሰማኛል” ብለዋል፡፡

XS
SM
MD
LG