ባለፈው ዓመት ከማዕከላዊ ጎንደር፣ ጭልጋ ወረዳ፣ አይከል ከተማ ተፈናቅለው ጎንደር አዘዞ የነበሩ ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው መመለስ መጀመሩን የማዕከላዊ ጎንደር ዞን አስታወቀ።
ተፈናቃዮቹ እየተመለሱ ያሉት ከኃይማኖት አባቶች፣ ከሀገር ሽማግሌዎች፣ ከምሑራን እና ከሌሎች የኅብረተስብ ክፍሎች ተውጣጥቶ የተቋቋመ ምክር ቤት ከነዋሪዎች ጋር ባደረገዉ ምክክር ከስምምነት ላይ በመደረሱ መሆኑን የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጠቅሷል። ወደ ቀድሞ ቀያቸው ሲመለሱ በከተማው ነዋሪዎች ደማቅ አቀባበልበመደረጉ የተደሰቱት ተፈናቃዮች ተከስቶ የነበረው ግጭት የጥቂት ፖለቲካ ነጋዴዎች ሴራ ነው ብለውታል።