በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢሰመኮ ሁሉም የሚዲያ አካላት በአስቸኳይ እንዲፈቱ ጠየቀ


ኢሰመኮ ሁሉም የሚዲያ አካላት በአስቸኳይ እንዲፈቱ ጠየቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:03 0:00

ኢሰመኮ ሁሉም የሚዲያ አካላት በአስቸኳይ እንዲፈቱ ጠየቀ

እስከ ትናንት ድረስ 16 ጋዜጠኞች በሕገ ወጥ መንገድ ታስረዋል ያለው ኢሰመኮ ሁሉም የሚዲያ አካላት በአስቸኳይ እንዲፈቱ ሲል ዛሬ ባወጣው መግለጫ ጠየ።

ከመግለጫው ጋር በተያያዘ ለቪኦኤ አስተያየታቸውን የሰጡት የኢሰመኮ የሕግና ፖሊሲ ሥራ ክፍል ዳይሬክተር ታሪኳ ጌታቸው፣ በእስር ላይ የሚገኙ ጋዜጠኞች እና ሌሎች የሚዲያ ሰራተኞች ሰብዓዊ መብታቸው ሊጠበቅ እንደሚገባ እና መጠየቅ ያለባቸውም በመገናኛ ብዙኃን ሕግ መሰረት እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

በተያያዘ ዜና በትናንትናው ዕለት በቁጥጥር ስር የዋሉት የፍትሕ መጽሔት ማኔጂንግ ዳይሬክተር ተመስገን ደሳለኝ እና የኢትዮ ፎረም አዘጋጅ ያየሰው ሽመልስ ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበው ተለዋጭ ቀጠሮ እንደተሰጠባቸው ጠበቆቻቸው ገልጸዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ሰቦንቱ አህመድ የተባለች የኤፍ.አይ.ቢ ቴለቪዥን ጋዜጠኛም ትናንት አመሻሽ ላይ በፖሊስ መያዟን የጣቢያው ዳይሬክተር ተናግረዋል፡፡

የሚዲያ ባለሙያዎች መታሰር እንደሚያሳስባቸው ዩናይትድ ስቴትስን ጨምሮ የተለያዩ አካላት የገለጹ ሲሆን፣ በፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ የኦፐሬሽን ዋና መምሪያ ኃላፊ አቶ ሙሊሳ አብዲሳ ትናንት ምሽት ለኢቢሲ በሰጡት ማብራሪያ፣ የሚዲያ ባለሙያዎች እስር ከሕግ ማስከበር እርምጃ ጋር የተያያዘ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

XS
SM
MD
LG