በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጋዜጠኞች ተመስገን ደሳለኝ እና ያየሰው ሽመልስ ታሰሩ


ጋዜጠኞች ተመስገን ደሳለኝ እና ያየሰው ሽመልስ ታሰሩ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:06 0:00

ጋዜጠኞች ተመስገን ደሳለኝ እና ያየሰው ሽመልስ ታሰሩ

የፍትሕ መጽሔት ማኔጂንግ ዳይሬክተር ተመስገን ደሳለኝ እንዲሁም የኢትዮፎረም አዘጋጅ ያየሰው ሽመልስ ዛሬ በፀጥታ ኃይሎች መያዛቸው ተገለጸ፡፡

ጋዜጠኛ ተመስገን ከቢሮው መያዙን አንድ ባልደረባው የገለጹ ሲሆን፣ ያየሰው ደግሞ ከቤቱ እንደተያዘ ጠበቃው ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡

ዩናይትድ ስቴትስ፣ በኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች መታሠር ጉዳይ እንዳሳሰባት የገለጸች ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ባለልጣናት በቅርቡ የታሠሩ ጋዜጠኞችን እና የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎችን በሙሉ መፍታት እንዳለባቸው - ዓለም አቀፉ የጋዜጠኛች መብት ተሟጋች ድርጅት ሲፒጄ ከትናንት በስቲያ መጠየቁ ይታወሳል።

ስለጋዜጠኞች መታሰር በኢትዮጵያ ባለስልጣናት በኩል በቀጥታ የተባለ ነገር ባይኖርም፣ በተለያዩ ወንጀሎች የተጠረጠሩ የተባሉ በርካታ ሰዎች መታሰራቸውን ግን ገልጿል፡፡

ዘገባው የኬኔዲ አባተ ነው።

XS
SM
MD
LG