በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሴኔጋሉ ሆስፒታል የእሳት አደጋ አዲስ የተወለዱ 11 ጨቅላ ህጻናት ሞቱ


ሴነጋል ውስጥ በሚገኝ አንድ ሆስፒታል በደረሰ የእሳት አደጋ፣ አዲስ ጨቅላ ልጇን ያጣች እናት
ሴነጋል ውስጥ በሚገኝ አንድ ሆስፒታል በደረሰ የእሳት አደጋ፣ አዲስ ጨቅላ ልጇን ያጣች እናት

ሴነጋል ውስጥ በሚገኝ አንድ ሆስፒታል በደረሰ የእሳት አደጋ፣ አዲስ የተወለዱ 11 ጨቅላ ልጆች መሞታቸውን የሴኔጋል ፕሬዚዳንት ማኪ ሳል ትናትን ረቡዕ በሰጡት መግለጫ አስታወቁ፡፡

ህጻናቱን የሞቱት ከአገሪቱ ዋና ከተማ በስተምስራቅ 120 ኬሎ ሜትር ርቀት ላይ ቲቫኡና በተባለች ከተማ በሚገኝ ማሜ አብዱ አዚዝ ሲ ዳባክ በተባለ ሆስፒታል የህጻናት ህክምና መስጫ ክፍል ውስጥ መሆኑን ፕሬዚዳንቱ ተናግረዋል፡፡

አንጎላን እየጎበኙ የነበሩት ፕሬዚዳንት ማኪ ሳል፣ ካሉበት ሆነው ባስተላለፉት መልዕክት፣ “ለህናጻቱ ቤተሰቦች የተሰማኝን ጥልቅ ሀዘን እገልጻለሁ” ብለዋል፡፡

የአደጋው መንስኤ ያልተገለጸ ሲሆን እየተጣራ መሆኑ በዘገባው ተጠቅሷል፡፡

XS
SM
MD
LG