በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዋግ ኽምራ የተከሰተውን በሽታ የሚያጣራ ዓለም አቀፍ ቡድን ወደ ስፍራው መላኩን ዞኑ አስታወቀ


ዋግ ኽምራ የተከሰተውን በሽታ የሚያጣራ ዓለም አቀፍ ቡድን ወደ ስፍራው መላኩን ዞኑ አስታወቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:49 0:00

ዋግ ኽምራ የተከሰተውን በሽታ የሚያጣራ ዓለም አቀፍ ቡድን ወደ ስፍራው መላኩን ዞኑ አስታወቀ

በአማራ ክልል ዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ውስጥ በህወሓት ቡድን ቁጥጥር ሥር ይገኛል በተባለው አበርገሌ ወረዳ 12 ቀበሌ በተለምዶ ፅላሪ ጀርገብ እየተባለ በሚጠራ ቦታ ተከስቷል የተባለውን መንስኤ የሚያጣራ ዓለም አቀፍ መርማሪ አካል ወደ ስፍራው መግባቱን ዞኑ አስታወቀ፡፡

መርማሪው አካል ጋር እስካሁን ግንኙነት አለማድረጋቸውን የዞኑ ጤና መምሪያ ኃላፊ ጠቁመው ልዑኩ አዲስ ከተከሰተው በሽታ ባሻገር ጦርነቱ ላስከተላቸው ሌሎች ሰብአዊና የጤና ጉዳቶች መፍትሄ ያመላክታል የሚል እምነት እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡

የዘጠኝ ዓመት ህፃናትን ህይወት የቀጠፈው በሽታ እንደተከሰተ አካባቢው በህወሓት ኃይሎች ቁጥጥር ስር በመሆኑ ጉዳዩን ለሚመለከታቸው አካላት ማሳወቃቸውን የአስተዳዳር ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ ዶ/ር ኪዳት አየለ ተናግረዋል።

ጉዳዩን ያሳወቁበት የጤና ሚኒስቴርም ቡድኑም ወደ ስፍራው ቡድን መላኩን እና ቡድኑም ተቀሰቀሰ ከተባለው የጤና ችግር ባሻገር በጦርነቱ ምክንያት ለተከሰቱ ሌሎች ሰብአዊ ቀውሶችና የጤና ችግሮችም መፍትሄ ያስቀምጣል የሚል እምነት እንዳላቸው ገልጸዋል።

የአሜሪካ ድምፅ ከቀናት በፊት በብሔረሰብ አስተዳዳር ዞኑ አበርገሌ ወረዳ ጽራሪ ጀርገብ አካባቢ የተቀሰቀሰው ወረርሽኝ በሦስት ቀናት ልዩነት ውስጥ ዘጠኝ ህፃናትን ለሞት ዳርጎ ወደሌሎች ቀበሌዎች እየተስፋፋ መሆኑን ነዋሪዎቹን እና አመራሮችን ጠቅሶ ዘግቦ ነበር፡፡

በዚህ ጉዳይ ላይ አስተያየት የሰጡት ዶ/ር ኪዳት ከመጀመሪዎያቹ ውጭ እስካሁን ተጨማሪ የሟቾች ቁጥር እንዳልደረሳቸውና ሥርጭቱም ከተቀሰቀሰበት አልፎ ወደሌሎች ቦታዎች በብዛት እንዳልተስፋፋ ከአካባቢው አገኘነው ያሉትን መረጃ አጣቅሰው ተናግረዋል፡፡

/ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ/

XS
SM
MD
LG