የሩሲያ ፓርላማ ትናንት ባወጣው ህግ፣ ምዕራባውያን አገሮች፣ የጸረ ሩሲያ ሚዲያ አቋም ካላቸው፣ አቃቢ ህግ በሞስኮ ቢሮ ያላቸውን የውጭ አገር ዜና ማሰራጫዎችን መዝጋት የሚያስችለውን ሥልጣን ሰጥቶታል፡፡
ህጉ የወጣው በምዕራብ ዓለም የሚገኙ አንዳንድ የሩሲያ መንግሥት የዜና ማሰራጫዎች መዘጋታቸውን ተከትሎ፣መሆኑ ተገልጿል፡፡
ባለፈው መጋቢት፣ ስለ ሩሲያ ጦር የሀሰት ዜናዎችን ማሰራጨት የሚያስቀጣ መሆኑን በመግለጽ በወጣው ህግ ላይ በተጨማሪነት የወጣው አዲሱ ህግ፣ በሩሲያ በሚገኙ የውጭ ዜና ማሰራጫዎች ላይ፣ ሌላ ጫና የሚፈጥር መሆኑ ተመልክቷል፡፡