በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

6750 ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞች ወደሀገራቸው ለመመለስ ማቀዱን የተመድ አስታወቀ


ፎቶ ፋይል፦ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በራስ አል አራ፣ ላህጅ፣ የመን ባህር ዳርቻ ከጀልባ ወረደው በእግራቸው ሲጓዙ እአአ ሐምሌ 26 ቀን 2019
ፎቶ ፋይል፦ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በራስ አል አራ፣ ላህጅ፣ የመን ባህር ዳርቻ ከጀልባ ወረደው በእግራቸው ሲጓዙ እአአ ሐምሌ 26 ቀን 2019

የተባበሩት መንግሥታቱ ዓለም አቀፍ የፍልሰተኞች ድርጅት ጦርነት ካዳሸቃት ከየመን ቢያንስ 6750 ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞችን በቀጣዮቹ ወራት ወደአገራቸው ለመመለስ ማቀዱን አስታወቀ። ዓለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት ፍልሰተኞቹን ለመመለስ ላወጣው ዕቅዱ ድጋፍ የሚሆን የሰባት ነጥብ አምስት ሚሊዮን ዶላር ዕርዳታ በዛሬው ዕለት ተማፅኗል።

አይኦኤም እአአ በዚህ 2022 ከስድስት መቶ የሚበልጡ ፍልሰተኞችን በሦስት በረራዎች ወደኢትዮጵያ እንዳጓጓዘ ገልጿል። ከመካከላቸው ስድሳው ካለአዋቂ ጠባቂ ብቻቸውን የነበሩ ልጆች መሆናቸውን አመልክቷል። አሁንም ከየመኗ የወደብ ከተማ ከአደን ወደ አዲስ አባባ ፍልሰተኞችን በአየር ለማጓጓዝ ማቀዱን ገልጿል።

በየመን የአይኦኤም ኃላፊ ክሪስታ ሮተንሽታይነር በየመን በኩል የሚያልፉት ወይም ማለፊያ መንገድ አጥተው የቀሩ ፍልሰተኞች እያሽቆለቆለ ባለው የየመን ሰብዓዊ ሁኔታ በከባዱ ከተጎዱት መካከል የሚጠቀሱ መሆናቸውን አውስተዋል።

የየመኑ የእርስ በርስ ጦርነት ወደሳውዲ አረቢያ ተሻግረው በቤት ሰራተኝነት ወይም በግንባታ ሥራ ተቀጥረው ለመስራት የሚጓጉ ፍልሰተኞችን የመን ከመግባት አላገዳቸውም። አይኦኤም እንዳለው ባለፈው እአአ 2021 ከአፍሪካ ቀንድ 27,700 ፍልሰተኞች ወደየመን እጅግ አስቸጋሪ የሆነውን ጉዞ አድርገዋል።

የመን እአአ ከ2014 ጀምራ በርስ በርስ ጦርነት ተጠምዳለች። ዘገባው የአሶሲየትድ ፕሬስ ነው።

XS
SM
MD
LG