በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጄነራል ተፈራ ማሞ “ሕገ መንግሥቱን በኃይል ለመናድ መሞከር” በሚል ወንጀል ተጠርጥረው ፍርድ ቤት ቀረቡ


ጄነራል ተፈራ ማሞ “ሕገ መንግሥቱን በኃይል ለመናድ መሞከር” በሚል ወንጀል ተጠርጥረው ፍርድ ቤት ቀረቡ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:13 0:00

ጄነራል ተፈራ ማሞ “ሕገ መንግሥቱን በኃይል ለመናድ መሞከር” በሚል ወንጀል ተጠርጥረው ፍርድ ቤት ቀረቡ

የቀድሞ የአማራ ክልል ልዩ ኃይል አዛዥ ብርጋዴል ጄነራል ተፈራ ማሞ “ሕገ መንግሥቱን በኃይል ለመናድ መሞከር” በሚል ወንጀል ተጠርጥረው ዛሬ ከሰዓት በኋላ ፍርድ ቤት መቅረባቸውን ጠበቃቸው አቶ ሸጋው አለበል ገለፀዋል።

በሌላ በኩል ደግሞ የአማራ ክልል መንግሥት በፋኖ ስም ከሚፈፀሙ ወንጀሎች ጋር በተያያዘ የተፈጠሩ ችግሮችን በመቀራረብና በመነጋገር ጭምር ለመፍታት መሞከር አለበት ሲሉ የቀድሞው የተቃዋሚ ፓርቲ አመራር አባልና የፓርላማ ተመራጭ አቶ መሀመድ አሊ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል። መንግስት የሰከነ አካሄድ መከተል እንዳለበትም አሳስበዋል።

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ይልቃል ከፋለ ከትላንት በስቲያ በሰጡት መግለጫ አስተዳደራቸው በፋኖ ስም እየተፈፀሙ ባሉ ወንጀሎች የተጠረጠሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር እያዋለ መሆኑን ገልፀዋል።

ይህ እርምጃ ፋኖን የማጥፋት ሳይሆን በፋኖ ስም የሚነግዱ ሕገወጦችን የመቆጣጠር ነው ሲሉ ርዕሰ መስተዳድሩ ለጋዜጠኞች መናገራቸው ይታወሳል።

/ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ያዳምጡ/

XS
SM
MD
LG