በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአማሮ ልዩ ወረዳ ሁለት አዳጊዎች በታጣቂዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ገለፁ


አማሮ ወረዳን የሚጠቁም የኢትዮጵያ ካርታ ከጎግል ማፕ ላይ
አማሮ ወረዳን የሚጠቁም የኢትዮጵያ ካርታ ከጎግል ማፕ ላይ

የኢትዮጵያ መንግሥት ሸኔ የሚላቸውና እራሳቸውን «የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት» ብለው የሚጠሩ ታጣቂዎች፤ በደቡብ ክልል አማሮ ልዩ ወረዳ ትፋተ ቀበሌ አደረሱ በተባለው ጥቃት ሁለት አዳጊዎች መገደላቸውን ቤተሰቦች ገለጹ።

ታጣቂዎች በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን እንደሚንቀሳቀሱ በስልክ ለአሜሪካ ድምፅ የገለጹት የወረዳው ነዋሪዎች እና ቤተሰቦቻቸው ከብቶቻቸው መዘረፉንም ተናግረዋል።

መንግሥት በታጠቁ ቡድኖች ላይ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን ቢገልፅም በወረዳው ሕዝብ ላይ የሚደረሰው ኢሰብዓዊ ጥቃት እና ጉዳት መቀጠሉን የልዩ ወረዳው የሰላም እና የፀጥታ ጽ/ቤት አስታውቋል።

ስሙ በተጠቀሰው በድን ላይ የቀረበውን ውንጀላ እና ክስ በተመለከተ ከቡድኑ የተገኘ አስተያየት የለም። ይሁንና የበድኑ ቃለ አቀባይ ከዚህ በፊት ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት አስተያየት ሠራዊታቸው በሲቪሎች ላይ ጥቃት እንደማያደርስ መግለፃቸው አይዘነጋም።

/ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ያዳምጡ/

በአማሮ ልዩ ወረዳ ሁለት አዳጊዎች በታጣቂዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ገለፁ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:01 0:00

XS
SM
MD
LG