በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ በሆቴል ሩዋንዳ ፊልም በጀግንነት የተዘከሩት ፖል ሩሴሳባጊና መታሰራቸው ተገቢ አይደለም አለች


ፋይል - በመቶዎች የተቆጠሩ ሰዎችን ከግድያ በማትረፋቸው ታሪካቸው ሆቴል ሩዋንዳ በተሰኘው በሆሊዉድ የተሰራ ፊልም የተሰራው ፖል ሩሴሳባጊና ኪጋሊ በሚገኘው ፍርድ ቤት ውስጥ ተቀምጠው
ፋይል - በመቶዎች የተቆጠሩ ሰዎችን ከግድያ በማትረፋቸው ታሪካቸው ሆቴል ሩዋንዳ በተሰኘው በሆሊዉድ የተሰራ ፊልም የተሰራው ፖል ሩሴሳባጊና ኪጋሊ በሚገኘው ፍርድ ቤት ውስጥ ተቀምጠው

ዩናይትድ ስቴትስ የሩዋንዳ መንግሥት በ”ሆቴል ሩዋንዳ” ፊልም በጀግንነት የተዘከሩትን ፖል ሩሴሳባጊናን ያሰራቸው ካለምክንያት ነው የሚል ድምዳሜ ላይ መድረሷን አስታወቀች፡፡


የዩናይትድ ስቴትስ ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ እና የቤልጂየም ዜግነት ያላቸው ፖል ሩሴሳባጊና የሩዋንዳ ፕሬዚደንት ፖል ካጋሜን “ አምባገነን” ብለው ማውገዛቸውን ተከትሎ በሽብርተኝነት ተከስሰው የሃያ አምስት ዐመት እስራት ቅጣት ተፈርዶባቸዋል፡፡


የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር መታሰራቸው ተገቢ አይደለም የሚል ድምዳሜ ላይ መድረሱን የገለፁት አንድ የሚንስቴሩ ቃል አቀባይ “ ከዚህ ድምዳሜ ላይ የተደረሰው አጠቃላይ ሂደቱን በተለይም ደግሞ በፍርድ ሂደቱ ወቅት የፍትሃዊ የፍርድ ሂደት ዋስትና ያልተሰጣቸው መሆኑን ከግንዛቤ በማስገባት እንደሆነ አመልክተዋል፡፡


የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር መታሰራቸውን አስመልክቶ ካሁን ቀደም ስጋቱን ገልጾ የነበረ ሲሆን እንዲፈቱ ለመጠየቅ ይህ ድምዳሜ ማስፈለጉን ገልጸዋል፡፡

በሩዋንዳ የዘር ፍጅት ወቅት በኪጋሊ የሚገኝ ሆቴል ስራ አስኪያጅ የነበሩት ፖል በመቶዎች የተቆጠሩ ሰዎችን ከግድያ በማትረፋቸው ታሪካቸው ሆቴል ሩዋንዳ በተሰኘው በሆሊዉድ የተሰራ ፊልም ተዘክሮላቸዋል፡፡

እ አ አ በ2020 ፖል ሩሴሳባጊና ወደቡሩንዲ ለመጓዝ የተሳፈሩበት አውሮፕላን ኪጋሊ አርፎ መታሰራቸው ይታወሳል፡፡ ዩናይትድ ስቲትስ የወሰደችው ድምዳሜ ሩዋንዳ እንድትለቅቃቸው በይበልጥ ግፊት እንድታደርግ ይረዳል ብሎ ቤተሰባቸው ተስፋ አድርጓል፡፡

XS
SM
MD
LG