በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሐረሪ ክልል ጋዜጠኛ ሙህዬዲን አብዱላሂ በዋስ መፈታቱን ገለፀ


የሐረሪ ክልል ጋዜጠኛ ሙህዬዲን አብዱላሂ
የሐረሪ ክልል ጋዜጠኛ ሙህዬዲን አብዱላሂ

‘ሕዝብን በመንግስት ላይ አነሳስተሃል’ በሚል ጥርጣሬ ከሳምንት በላይ ታስሮ የቆየው የሐረሪ ክልል ጋዜጠኛ ሙህዬዲን አብዱላሂ በ2 ሺ ብር ዋስ መፈታቱን ገለፀ።

በሀረሪ ቲቪ የኦሮምኛ የመዝናኛ ፕሮግራም አርታዒ ሙሄዲን ጎንደር ውስጥ በሙስሊሞች ላይ ተፈጽሞ የነበረውን ጥቃት በተመለከተ በግል ፌስቡክ ገፁ ላይ ባሰፈረው ጽሑፍ ምክኒያት እንደታሰረም ገልጿል።

እስካሁን ክስ እንዳልተመሰረተበት የሚናገረው ሙህዬዲን የተጠረጠረበት ወንጀል ሕዝብን በመንግስት ላይ ማነሳሳት እንደሆነ እንደተነገረው፣ ሆኖም በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን የተለያዩ ክሶች እንደቀረቡበት ተደርጎ መዘገቡን ተናግሯል።

ለስምንት ቀናት በቁጥጥር ስር የቆዬው ጋዜጠኛው አመራሮች ቢሮ ድረስ ጠርተው የዋስትና ጥያቄ ማቅረብ እንደሚችል ነግረውት ጥያቄውን ማቅረቡንና በታሰረ በዘጠነኛው ቀን በ2ሺ ብር ዋስ መፈታቱን ለአሜሪካ ድምጽ ገልጿል። ግንቦት 17 ቀን የፍርድ ቤት ቀጠሮ እንዳለው እና የክሱ ሂደትም ገና በምርመራ ላይ እንደሚገኝም ተናግሯል።

ዘገባው የአዲስ ቸኮል ነው።

XS
SM
MD
LG