“የተጀመረው እርምጃ ፋኖን የማጥፋት ሳይሆን በፋኖ ሰም የሚነግዱ ሕገወጦችን የመቆጣጠር ነው ሲሉ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተደድር ዶ/ር ይልቃል ከፋለ ተናግረዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ ዛሬ በሰጡት መግለጫ፤ በክልሉ ውስጥ የሚታዩ ስር የሰደዱ ሕገ ወጥ ተግባራትን እና ሥርዓት አልበኝነትን ለመቆጣጠር የሕግ ማስከበር እንቅስቃሴ ተጀምሯል ብለዋል።
ከአማራ ክልል ውጭ ሰለሚታሠሩ ሰዎች ጭምር ያነሡት ርዕሰ መስተዳድሩ ከመካከላቸው የደረሱበት የማይታወቅ መኖራቸውን በመጥቀስ ሁኔታው ስህተት መሆኑን እና መታረም እንደሚገባው ጠቁመዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ መግለጫውን የሰጡት በአንዳንድ የክልሉ አካባቢዎች እስራቶች እየተካሄዱ መሆኑን የሚጠቁሙ መረጃዎች እየወጡ ባሉበት ወቅት ነው።
ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።