በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ወደ ትግራይ እየገባ ያለው እርዳታ ከሚያስፈልገው አምስት በመቶ ብቻ መሆኑን ክልሉ ገለፀ


ፎቶ ፋይል፦ መቀሌ ከተማ
ፎቶ ፋይል፦ መቀሌ ከተማ

የተኩስ ማቆም ሥምምነት ከተደረገ ወዲህ ወደ ክልሉ 430 እርዳታ የጫኑ ተሽከርካሪዎች መግባታቸውንንና ይህም የክልሉ ሕዝብ ከሚያስፈልገው 5 በመቶ ብቻ መሆኑን ትግራይ ክልል አስታወቀ።

የክልሉ ገጠርና ግብርና ቢሮ አስቸኳም ምላሽ ዳይሬክተር አቶ ገብረ እግዚያብሔር አረጋዊ፤ በአሁኑ ሰዓት የእርዳታ ፈላጊ ሰዎች ቁጥር መጨመሩንና በቅርቡ በተደረገ ዳሰሳ ጥናትም 6.5 ሚሊዮን ሕዝብ እርዳታ እንደሚያስፈልገው ቢሮው ገልጿል።

በሌላ በኩል በቅርቡ የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ደበበ ዘውዴ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ባደረጉት ጥናት በትግራይ ያሉ እርዳታ ፈላጊዎች ቁጥር 5.2 ሚሊዮን እንደሆነ፣ ወደትግራይም በረድዔት ሥራ ላይ የተሰማሩ 92 ዓለም አቀፍ ድርጅቶች እንዳሉ፣ የኢትዮጵያ መንግሥትም የረድዔት ድርጅቶቹ አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ምቹ ሁኔታዎች መፍጠሩን ተናግረው ነበር።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ይከታተሉ።

ወደ ትግራይ እየገባ ያለው እርዳታ ከሚያስፈልገው አምስት በመቶ ብቻ መሆኑን ክልሉ ገለፀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:38 0:00

XS
SM
MD
LG