የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ፕሬዚዳንት ካማላ ሃሪስ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን በሞት ለተለዩት የተባበሩት የአረብ ኤሚሬቶች ፕሬዚዳንት ቤተሰብ ሀዘናቸውን ገለጹ።
ምክትል ፕሬዚዳንት ሃሪስ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ብሊንከን በመካከለኛው ምስራቅ ብቻ ሳይሆን ከክልሉም ውጭ ተጽዕኖ ፈጣሪ ከሆኑት ከሟቹ ፕሬዚዳንት ወንድም ከአዲሱ ፕሬዚዳንት ሼኽ መሀመድ ቢን ዛይድ አል ኔህያን ጋር ተገናኝተዋል።
ምክትል ፕሬዚዳንት ሃሪስ ከአዲሱ ፕሬዚዳንት ጋር የዩናይትድ ስቴትስ ጥሩ ወዳጅ እና ከበርካታ የዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደሮች ዘንድ ታማኝ አጋር የነበሩትን ሼኽ ኻሊፋን በማስታወስ መወያየታቸውን እና አዲስ ተመራጩን ፕሬዚዳንት በመመረጣቸው እንኳን ደስ ያለዎ ማለታቸውን ከምክትል ፕሬዚዳንቷ ጽህፈት የወጣው መግለጫ አስታውቋል።
በማስከተል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ብሊንከን ከኤሜሬቱ አቻቸው ሼኽ አብዱላሂ ቢን ዛይድ አል ኔህያን ጋር ለእራት መገናኘታቸው ተገልጿል።