በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ አማጺያን 10 ሰዎችን መግደላቸውን ተመድ አስታወቀ


የመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ ካርታ/ቪኦኤ/
የመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ ካርታ/ቪኦኤ/

በመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ አማጺያን 10 ሰላማዊ ሰዎችን መግደላቸውን በሀገሪቱ ውስጥ ያለው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰላም አስከባሪ ኃይል ቃል አቀባይ ተናገሩ።ግድያው የተፈጸመው ከሀገሪቱ መናገሻ ከተማ ባንጉዌ በሰሜን ምስራቅ በሚገኝ ስፍራ እንደሆነም ቃል አቀባዩ ለኤ ኤፍ ፒ ተናግረዋል።

"አንድነት ለመካከለኛው አፍሪካ ሰላም የተባለው ቡድን ፣ በምህጻሩ ዩፒሲ የታጠቁ ኃይሎች፣ በህዝብ ዘንድ የመብት ጥሰት ፈጽመዋል፣ አስር ሰዎችንም ( ቦኮሎቦ በተባለ መንደር ውስጥ) ባለፈው ሰኞ ገድለዋል “ ብለዋል፣ አብዱል አዚዝ ኦዬድራጎ የተሰኙት የተባሉት ቃል አቀባይ ።

እኒሁ ታጣቂዎች በቀደመው ጊዜ የጸጥታ ኃይሎችን ማጥቃታቸውን ቃል አቀባዩ አክለዋል። ተጨማሪ ማብራሪያ ከመስጠት ግን ተቆጥበዋል ። ከእነዚህ የጭካኔ ተግባራት በኃላ የሰላም አስከባሪ ኃይሉ የሞሪታኒያ ሰማያዊ መለዮ ለባሾችን በአስቸኳይ ወደ ስፍራው በመላክ ህዝቡን ለመጠበቅ እንደተንቀሳቀሰ ኦዬድራጎ ተናግረዋል።

ከባንጉዌ 400 ኪሎሜትሮች ወደሚርቀው ስፍራ ከኔፓል ጦር የተውጣጣው ሁለተኛው ቡድን መላኩን ቃል አቀባዩ ተናግረዋል። ጥቃቱን እንደፈጸመ የተነገረው ታጣቂ ቡድን ዩፒሲ ጦር መሪ ፣ ፕሬዚደንት ፋውስቲን አርቻንግ ታውዴራን ከስልጣን ለማውረድ በጎረጎሳዊያኑ 2020 የተመሰረተው የአርበኞች ቅንጅት ለለውጥ የተሰኘው የአማጺያን ቡድኖች ትብብር መምሪያ ኃላፊ አሊ ዳራሳ በበኩላቸው ፣ የሰኞ ዕለቱን ጭፍጨፋ አውገዘዋል።እሳቸው 27 የፉላኒ ጎሳ አባላትን ጨምሮ 30 ያህል የእስልምና ዕምነት ተከታዮች በሩሲያ ቅጥር ተዋጊዎች እና የፕሬዚደንግ ታውዴራ ክንፍ በሆነው የጸረ -ባላካ ታጣቂዎች መገደላቸውን ገልጸዋል።

ከዓለም ደሃ ሀገራት መካከል በሁለተኛ ደረጃ ላይ የምትገኘው የመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ፣ ከጎረጎሳዊያኑ 2013 ጀምሮ የእርስ በእርስ ጦርነት አውድማ ሆናለች ።

XS
SM
MD
LG