በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ወደ ትግራይ ክልል እየገባ ያለው እርዳታ በቂ አይደለም ተባለ


ወደ ትግራይ ክልል እየገባ ያለው እርዳታ በቂ አይደለም ተባለ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:47 0:00

ወደ ትግራይ ክልል እየገባ ያለው እርዳታ በቂ አይደለም ተባለ

ባለፈው ሳምንት የእርዳታ አቅርቦት የጫኑ 165 ተሽከርካሪዎች ወደ ትግራይ ክልል መድረሳቸውንና 94 ተሽከርካሪዎች ደግሞ በጉዞ ላይ መሆናቸውን የዓለም የምግብ ፕሮግራም አስታውቋል።

የድርጅቱን መረጃ ያረጋገጡት የኢትዮጵያ አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ደበበ ዘውዴ፣ ከዚህም ውጭ በአየር እና በየብስ የሚደረገው የእርዳታ አቅርቦት መቀጠሉን አብራርተዋል፡፡

ይሁን እንጂ ወደ ትግራይ ክልል እየገባ ያለው የዕርዳታ አቅርቦት ከሚያስፈልገው አንጻር እጅግ አነስተኛ መሆኑን እና በዚህም ምክንያት ሞትና ረሃብ እየተስፋፋ እንደሚገኝ የትግራይ ክልል የግብርና እና ገጠር ልማት ቢሮ ኃላፊ መሆናቸውን የገለጹት ዶ/ር አትንኩት መዝገቡ፣ በቅርቡ ለቪኦኤ ተናግረዋል፡፡

ወደ ክልሉ ለሚደረገው የዕርዳታ አቅርቦት ማነስ የትግራይ ክልል አመራሮች እና አንዳንድ የረድኤት ድርጅቶች መንግሥትን ተጠያቂ ቢያደርጉም፣ መንግስት ግን ውንጀላውን አይቀበልም፡፡

XS
SM
MD
LG