በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ለረጅም ጊዜ በህመም ላይ የነበሩት የተባበሩት የአረብ ኤሚሬቶች መሪ አረፉ


የተባበሩት የአረብ ኤሚሬቶች የረጅም ጊዜ መሪ ሼኽ ኻሊፋ ቢን ዛዪድ ናህያን
የተባበሩት የአረብ ኤሚሬቶች የረጅም ጊዜ መሪ ሼኽ ኻሊፋ ቢን ዛዪድ ናህያን

የተባበሩት የአረብ ኤሚሬቶች የረጅም ጊዜ መሪ ሼኽ ኻሊፋ ቢን ዛዪድ ናህያን በዛሬው ዕለት በሰባ ሦስት ዓመታቸው አረፉ።

የተባበሩት ኤሚሬቶች የፕሬዚዳንታዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር ለአርባ ቀናት የሚቆይ የሀዘን ጊዜ አውጇል፡፡ በዚሁ የሀዘን ጊዜ ለሦስት ቀናት የመንግሥትም የግል መሥሪያ ቤቶችም ዝግ ይሆናሉ፡፡

የሀገሪቱ ባንዲራ ዝቅ ብሎ ይውለበለባል ብሏል፡፡ ዜና ዕረፍታቸውን ተከትሎ ከአካባቢው ሀገሮች በቀዳሚነት አቡ ዳቢ ከምትደግፋቸው የአረብ ሀገሮች መሪዎች እና ከመላው ዓለም የሀዘን መግለጫ እየጎረፈ መሆኑ ተዘግቧል፡፡

ሀገራቸውን ከነበረባት የእዳ ጫና አላቅቀው ታላቅ የአኪኖሚ ዕድገት የመሩዋት ፕሬዚዳንቷ ሼክ ኻሊፋ ቢን ዛዪድ አል ናህያን ከዓለም በሰማይ ጠቀስነቱ ወደር የሌለው ህንጻ “ቡርጅ ኻሊፋ” በስማቸው ተሰይሞላቸዋል፡፡

ሼክ ኻሊፋ እ አ አ በ2014 ባጋጠማቸው የአንጎል ውስጥ ደም መፍሰስ አጣዳፊ የቀዶ ጥገና ህክምና ከተደረገላቸው ወዲህ ዕለታዊ የአመራር ሥራቸውን ትተው ቆየተዋል፡፡

XS
SM
MD
LG