በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ትግርኛና አፋን ኦሮሞ በጉግል ቀጥታ ትርጉም ውስጥ ገቡ


ጉግል 24 የአፍሪካ ቋንቋዎች ተናጋሪዎች መድረኩን በቀላሉ መጠቀም እንዲችሉ የቀጥታ ትርጉም አገልግሎት ውስጥ ያካተታቸው መሆኑን አስታውቋል።

ግዙፉ የኢንተርኔት ላይ መቅዘፊያ ጉግል ከትናንት በስተያ ረቡዕ ባወጣው መግለጫ ቀደም ሲል አገልግሎት ሲሰጥባቸው በቆዩ ቋንቋዎች ላይ አፋን ኦሮሞና ትግርኛን መጨመሩን አመልክቷል።

በዓለምአቀፍ ደረጃ በ133 ቋንቋዎች የቀጥታ ትርጉም አገልግሎት የሚሰጠው ጉግል አፋን ኦሮሞና ትግርኛ በቴክኖሎጂው ዘርፍ በቂ ትኩረትና ሽፋን ሳይሰጣቸው መቆየቱን ጠቁሟል።

ሁለቱን ጨምሮ ሰሞኑን የተጨመሩ ቋንቋዎች በዓለም ዙሪያ 300 ሚልዮን ሰው የሚጠቀምባቸው መሆኑን ጉግል ባወጣው መረጃ ገልጿል።

XS
SM
MD
LG