በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ ፍ/ቤት ዳኞች ዛሬ በዝግ ይሰበሰባሉ


 የዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት
የዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት

ዘጠኙ የዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች ጽንስ ማቋረጥን የሚመለከተው ረቂቅ ሰነድ በድብቅ ከወጣ ወዲህ ዛሬ ለመጀመሪያ ጊዜ በግል በዝግ ይሰበሰባሉ፡፡ አስቀድሞ በእቅድ ተይዞ የነበረ ስብሰባ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በቅርቡ ሾልኮ የወጣው የውሳኔ ረቂቅ አስተያየታቸው “ሮ ቪ ዌድ” በሚል ምህጻር የሚጠራውን ጽንስ ማቋረጥን በሀገር አቀፍ ደረጃ የሴቶች ህጋዊ መብት ያደረገውን የፍርድ ቤቱን ውሳኔ በመቀልበስ ቢያንስ ግማሽ በሚሆኑት የሀገሪቱ ክፍላተ ሀገር ጽንስ ማቋረጥን በጥብቅ እንዲገደብ ያደርጋል፡፡

የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ዳኞች የተዋበው የዝግ ስብሰባ አዳራሽ የሚያደርጉት ጉባኤ ውጥረት የተመላበት ሊሆን እንደሚችል ተጠቁሟ፡፡ ከዳኞቹ በስተቀር ሌላ አንድም ሰው ዝር አይልም፡፡

ከሁሉም በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ዳኝነት ዘመናቸው አዲስ የሆኑት ዳኛ ኤሚ ኮኒ ባረት የስብሰባውን ቃለ ጉባኤ እንዲይዙ ኃላፊነት ተሰጥቷቸዋል፡፡ ዳኞቹ ስብሰባቸውን የሚያካሂዱት የሴቶች ጽንስ የማቋረጥ መብት የወደፊት እጣ ፈንታ ምን እንደሚሆን ረቂቅ አስተያየታቸውን የያዘውን ሰነድ ማን በድብቅ እንዳወጣው ምርመራ እየተካሄደ ባለበት አስጨናቂ ወቅት ነው፡፡

XS
SM
MD
LG