በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአሜሪካ ምክርቤት ለዩክሬን ርዳታ የሚውል ተጨማሪ 40 ቢሊየን ዶላር አፀደቀ


የአሜሪካ ምክርቤት ለዩክሬን ርዳታ የሚውል ተጨማሪ 40 ቢሊየን ዶላር አፀደቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:15 0:00

የአሜሪካ ምክርቤት ለዩክሬን ርዳታ የሚውል ተጨማሪ 40 ቢሊየን ዶላር አፀደቀ

ዩናይትድ ስቴትስ ራሽያ በዩክሬን ላይ የከፈተችውን ጦርነት ለመመከት የምታደርገው ጥረት በፍጥነት እያደገ ሲሆን ማክሰኞ እለት የሀገሪቱ ተወካዮች ምክር ቤት ለዩክሬን አዲስ ወታደራዊ እና ሰብዓዊ ርዳታ እንዲውል ያፀደቀውን 40 ቢሊየን ዶላር የህግ መወሰኛ ምክር ቤቱ በዚህ ሳምንት መጨረሻ ያሳልፈዋል ተብሎ እየተጠበቀ ነው። ይህም የጦር መሳሪያዎችን በፍጥነት ወደ ዩክሬን ለመላክ እንዲያስችል የታቀደውን አዲስ የብድር ፕሮግራም ተከትሎ የቀረበ መሆኑ ተገልጿል።

በኦዴሳ እና ሌሎች የዩክሬን ከተሞች የሚካሄደው ጦርነት እየተጋጋለ በሄደበት ወቅት፣ ዩናይትድ ስቴትስ ለሀገሪቱ የምታደርገው ርዳታም እንዲሁ ታይቶ በማያውቅ ሁኔታ እየጨመረ ነው።

የዩናይትድስቴትስ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለዩክሬን ርዳታ የሚውል 13.6 ቢሊየን ዶላር ባፀደቀ በሁለት ወር ውስጥ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን፣ ለወታደራዊ ርዳታ የሚውለው ገንዘብ በሳምንት ውስጥ እንደሚያልቅ በማስጠንቀቅ ተጨማሪ 33 ቢሊየን ዶላር እንዲጨመር ጠይቀው ነበር።

"ጦርነቱ የሚያስወጣው ወጪ ትንሽ አይደለም። ነገር ግን ለጠብ ጫሪ እጅ መስጠት ደግሞ ዋጋው እጅግ የበዛ ነው። ለዛ ነው በዚህ ሁኔታ ውስጥ የምንቆየው። "

ይህ በእንዲህ እንዳለ የዩናይትድ ስቴት ከፍተኛ የደህንነት ባለስልጣን፣ የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ለረዘመ ጦርነት እየተዘጋጁ መሆኑን እና በዩክሬን እየተደረገ ያለው ጦርነት ያለውጥ ባለበት እየቀጠለ መሆኑን ገልፀዋል።

ተጨማሪ እንዲሆን የተጠየቀው 33 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር በቂ አይደለም ያሉት ዲሞክራቶች ደግሞ ሌላ 7 ቢሊየን ዶላር እንዲጨመር አድርገዋል። የዲሞክራት ተመራጩ ሴናተር ክሪስ መርፊ ይህን ይላሉ -

"ራሽያ ገንዘቧን መጨረሷ አይገርም። መከላከያ መሳሪያዎቿም ያልቃሉ። እኛ ደግሞ ዩክሬን ገንዘብም የመከላከያ መሳሪያም እንዳያልቅባት ማረጋገጥ አለብን።"

በሳምንቱ መጀመሪያ ፕሬዝዳንት ባይደን፣ በሁለተኛው አለም ጦርነት ወቅት ፀድቆ ከነበረውና የአውሮፓ ሀገራት የጀርመኑን ናዚ እንዲያሸንፉ የረዳቸው ህግ ጋር የሚመሳሰል ረቂቅ ህግ በፊማቸው አፅድቀው ነበር።

ይህ አዲስ ህግ ፕሬዝዳንቱ የጦር መሳሪያዎችን በተፋጠነ መልኩ ወደ ዩክሬን መላክ እንዲችሉ የሚያግዛቸው ሲሆን አንዳንድ ጉዳዩ የሚከታተሉ ተንታኞች ግን ይህ በሪፐብሊካን እና በዲሞክራት የህዝብ ተወካዮች እየተደገፈ ያለ 'የጦረኝነት ባህሪ' ነው ሲሉ እያስጠነቀቁ ነው።

ከነዚህ አንዱ ኩዊንሲ የተሰነ የመንስት ስራን በሀላፊነት መውጣት የሚከታትል ተቋም ዳይሬክተር የሆኑት ጆርጅ ቢቢ ናቸው።

"ለዩክሬን እየተደረገ ያለው አይነት ገደብ የሌለው፣ የት ጋር እንደሚያቆም የማይታቀቅ ወታደራዊ ድጋፍ ሊያመጣው የሚችለው ውጤት እና በተለይ ደግሞ የአሜሪካ ህዝብ ደህንነት አደጋ የደቀነ ጦርነትን ሊያራዝም የሚችል እየታወቀ፣ ይሄ በዋሽንግተን በትኩረት ክርክር ሊደረግበት ሲገባው ግን እድሉን ያላገኘ ርዕሰጉዳይ ይመስለኛል።"

በዚህ መሀል ግን የህዝብ ተዋካዮች ምክር ቤት ኮቪድ 19ን ለመዋጋት በተጠየቀው 22.5 ቢሊየን ዶላር ላይ መስማማት አልቻለም። ይህ ገንዘብ በዓለም አቀፍ ደረጃ ወረርሽኙን ለመዋጋት የተጠየቀውን 5 ቢሊየን ዶላር የሚያጠቃልል ሲሆን ገንዘቡ ለዩክሬን ከተጠየቀው ገንዘብ ተነጥሎ እንዲቀር መደረጉን የሪፐብሊካኑ ተመራጭ ሴናተር ጄምስ ሪች ይገልፃሉ።

"ሁለቱ እንዲነጣጠሉ የተደረገው የዩክሬን ጉዳይ በፍጥነት እንዲያልቅና ወደፊት እንዲሄድ ስለፈለግን ነው። ይሄ በምንም መልኩ የኮቪድን ጥያቄ የማሳነስ ጉዳይ ተደርጎ ሊታይ አይገባም። ነገር ግን እኔ እንደሚመስለኝ በአሁኑ ሰዓት የዩክሬን ጉዳይ ከኮቪድ የበለጠ በፍጥነት እና በከፍተኛ ሁኔታ እየጎዳን ነው።"

ይህ በእንዲህ እንዳለ የጣሊያኑ ጠቅላይ ሚኒስቴር ማሪዮ ድራጊ አውሮፓውያን ለግጭቱ ዲፕሎማሲያዊ መፍትሄ ማግኘት እንደሚፈልጉ የሚገልፅ መልዕክት በመያዝ ማክሰኞ እለት በዋይት ኃውስ ተገኝተው ነበር።

"ህዝቡ የሚያስበው፣ ወይም ማሰብ የሚፈልጉት ቢያንስ ተኩስ የማቆም ስምምነት መደርስ የሚችልበት ሁኔታ እንዳለ እና እምነት የሚጣልበት ድርድር እንደገና እንደሚጀመር ነው።"

ባይደን የድራጊን አስተያየት የሚያንፀባርቅ ምላሽ አልሰጡም፣ ሆኖም የዩናይትድ ስቴትስ ባለስልጣናት ሩሲያ ለመነጋገር ፈቃደኛ ልትሆን ትችላለች በሚለው ሀሳብ ላይ ጥርጣሬያቸውን ገልፀዋል።

XS
SM
MD
LG