በደቡብ ክልል ደራሼ ወረዳ ውስጥ መሳሪያ ታጥቀው ይንቀሳቀሳሉ የተባሉ ታጣቂዎች እጃቸውን እንዲሰጡና ትጥቃቸውን እንዲፈቱ በአካባቢው የተቋቋመው ኮማንድ ፖስት የሰጠው ጊዜ ገደብ ማብቃቱን ተከትሎ በመንግሥት ወታደሮችና በታጣቂዎቹ መካከል የተኩስ ልውውጥ መደረጉን የልዩ ወረዳው ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ። ነዋሪዎቹ ፈርተው ከአካባቢው በመሸሽ ጫካ ውስጥ እንደሚገኙ ተናግረዋል።
በአካባቢው የተቋቋመው ወታደራዊ ዕዝ ጥምር ኃይል ምክትል ሰብሳቢ ሌተናል ኮሎነል ፈጥነ ሲሳይ ታጣቂዎቹ የተሰጠውን የጊዜ ገደብ ተጠቅመው እጃቸውን የማይሰጡ ከሆነ እዙ እርምጃ እንደሚወስድ ማስታወቃቸውን የክልሉ የመንግትሥ ቴሌቪዥኝ ጣቢያ ዘግቧል።
ዮናታን ዘብዲዮስ ዘገባ ነው።