በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጆን ሊ የሆንግ ኮንግ መሪ ሆነው ተመረጡ


ጆን ሊ
ጆን ሊ

በሆንግ ኮንግ በተካሄደ ምርጫ ጆን ሊ 99 በመቶ የቤጂንግ ምርጫ ኮሚቴን ድምጽን በማግኘት ተመርጠዋል። ዛሬ ጠዋት በተካሄደው ምርጫም ጆን ሊ በ 1416 የተመረጡ ሲሆን ይህም ለማሸነፍ ከሚያስፈልጋቸው ድምጽ በ 751 የላቀ ነው። በምርጫው ውስጥ ብቸኛ ተወዳዳሪ የነበሩት ጆን ሊ በተለይም ባለፈው ወር ላይ የቤጂንግን ይሁንታ ማግኘታቸው ከተረጋገጠ በኋላ ማሸነፋቸው የታወቀ ነበር።

ሊ ከአሁኗ መሪ ኬሪ ላም እ.ኤ.አ በመጪው ሃምሌ አንድ 2022 ስልጣን ይረከባሉ። ላም ሊ በመመረጣቸው የእንኳን ደስ አሎት መልዕት ያስተላለፉ ሲሆን የምርጫውን ውጤት ወደ ቤጂንግ አስተላልፋለሁ ብለዋል።

ይሁን እንጂ የዚህ ምርጫ ውጤት ቤጂንግ በቀጣይ በሆንግ ኮንግ ላይ ያላትን ጫና ልታጠብቅ ትችላለች በሚል ስጋትን አጭሯል። ይህም ሊ አብዛኛውን የስራ ዘመናቸውን ባሳለፉበት የፖሊስ እና የጸጥታ ቢሮ ውስጥ እ.ኤ.አ በቤጂንግ ላይ የተጣለውን የጸጥታ ሕግን በመደገፍ በጉልህ የሚናገሩ ሰው መሆናቸው ነው።

ሊ እ.ኤ.አ በ2019 ዓ.ም ለተቃውሞ የወጡ ሰዎች ላይ ፖሊስ አስለቃሽ ጭስ እና የፕላስቲክ ጥይት እንዲተኮስ በማድረግ ብዙዎች ተከበው እንዲታሰሩ የሚያደርገውን ተልዕኮ በመምራታቸው ታዋቂ ሊሆኑ ችለዋል።

ይህንኑ ተቃውሞ ተከትሎም በዛኑ ዓመት የኮቪድ 19 ወረርሽኝ በነገሰበት የውጪ ሃገራት ዜጎች እና እጅግ የተማሩ ብዙዎችን ጨምሮ 7.4 ሚሊየን ሰዎች በወረርሽኙ መሃከል ከተማዋን ለቀው ወጥተዋል።

XS
SM
MD
LG