በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሜጀር ጀነራል ገ/መድህን ፈቃዱ የቀብር ሥነ ስርዓት ዛሬ በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ተፈጸመ


ሜጀር ጀነራል ገ/መድህን ፈቃዱ
ሜጀር ጀነራል ገ/መድህን ፈቃዱ

በእስር ላይ እያሉ ጠያቂ ቤተሰቦቻቸው ፊት ተዝለፍልፈው በመውደቅ ከደቂቃዎች በኋላ ሕይወታቸው ያለፈው የቀድሞ የመከላከያ ሚኒስቴር የኮሚኒኬሽን ኤሌክትሮኒክስ ሳይበር መምሪያ ኃላፊ ሜ/ጀ ገብረመድህን ፍቃዱ የቀብር ሥነ ስርዓት ዛሬ በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ተፈፅሟል።

በከፍተኛ የሀገር ክህደት ወንጀል ክስ ቀርቦባቸው በእስር ላይ ሆነው ጉዳያቸውን በፍርድ ቤት በመከታተል ላይ የነበሩት የሜጀር ጀነራል ገ/መድህን ሕይወታቸው ያለፈው ሰኞ ሚያዝያ 24/2014 ዓ.ም ነው።

የሜጀር ጀነራል ሕይወት ማለፍን በተመለከተ የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ከትናንት በስቲያ በፌስቡክ ገጹ ባወጣው አጭር መግለጫ፣

“ከረፋዱ ሦስት ሰዓት ተኩል አካባቢ በቤተሰብ ጥየቃ ሰዓት ባለቤታቸው እና ልጃቸው አስጠርተዋቸው እያወሩ እያለ በድንገት በመውደቃቸው ወዲያውኑ ከቤተሰቦቻቸው ጋር ወደ ሕክምና ቦታ ቢወሰዱም ህይታቸው አልፏል” ሲል ማስታወቁ ይታወሳል።

የቀብር ሥነ ስርዓት አዘጋጅ ኮሚቴ አባል አቶ ሰሎሞን አብራሃ በሜጀር ጀነራል ገ/መድህን የቀብር ሥነ ስርዓት ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስትያን ፓትርያርክ አቡነ ማቲያስን ጨምሮ ሌሎች እንግዶች መገኘታቸውን ለአሜሪካ ድምፅ ገልፀዋል።

ሜጀር ጀነራል ገብረ መድህን በተከሰሱበት የክስ መዝገብ አብረዋቸው የተከሰሱት ተከሳሾች አጃቢ ተመድቦላቸው መቅበር እንዲችሉ ፍርድ ቤቱን መጠየቃቸውን በትናንትናው ዕለት መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን ፍርድ ቤቱ ጥያቄውን ውድቅ በማድረጉ ተከሳሾቹ በቀብሩ ሥነ ስርዓት ላይ መገኘት እንዳልቻሉ አቶ ሰሎሞን ጨምረው ገልፀዋል።

በሌላ በኩሉ በቀብሩ ሥነ ስርዓት የተገኙ ወጣቶች፣ ‘ትግራይ ታሸንፋለች’፣ ፈጽሞ አንምበረከክም’ የሚሉ እና ሌሎች መፈክሮች ያሰሙ እንደነበር፣ ለጥበቃ ከተሰማራው የፖሊስ ኃይል ጋር ወደ ግጭት እንዳልተገባ ይሁንና የውጥረት መነሻ ሆኖ እንዳለፈ የቀብሩ አስተባባሪ ሰሎሞን አብርሃ ገልፀውልናል።

XS
SM
MD
LG