የዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ ናንሲ ፔሎሲ፣ እና አራት ዴሞክራት የኮንግረስ አባላት የዩክሬንን መናገሻ ከተማ ኪቭን ቅዳሜ ዕለት ጎብኝተዋል ።ከዩክሬንን ፕሬዚደንት ቭሎድሜር ዘለንስኪ ጋር ተገናኝተውም ተነገራርዋል ።
ጉብኝቱ ዩክሬንን ለነጻነት ስለምታደርገው ፍልሚያ ለማመስገን፣ ፍልሚያው እስኪጠናቀቅ ዩናይትድ ስቴትስ ያላትን የድጋፍ ቁርጠኝነት ለማረጋገጥ ያለመ መሆኑን ፔሎሲ ለዘለንሲክ ነግረዋቸዋል ።
ከፔሎሲ ጋር ወደ ዩክሬን ያቀኑት ፣ የህዝብ እንደራሴዎች - የካሊፎርኒያው አዳም ሼፍ፣ የማሳቹሴቱ ጂም ማክገቨርን ፣ የኒዮርኩ ግሪጎሪ ሚክስ እና የኮሎራዶው ጄሰን ክሮ ናቸው ።
ይህ በእንዲህ እያለ ቅዳሜ ዕለት በኦዴሳ የአየር ማረፊያ ላይ በደረሰ የሩሲያ የሚሳኤል ጥቃት የአየር ማኮብኮቢያው ጎዳና መውደሙን የዩክሬን ጦር ይፋ አድርጓል ።
ለሲኤን ኤን ኤን ምስክርነቷን የሰጠች አንድ ግለሰብ ፣በደቡባዊቷ ከተማ ሰማይ ላይ ቢያንስ አንድ ተዋጊ አውሮፕላን መመልከቷን ፣ የአደጋ ጊዜ ደዋል ከተሰማ በኃላ መላ ከተማዋ በፍንደታ መናጧን ተናግራለች ።
ሩሲያ የዩክሬንን ምስራቃዊ የዶንባስ ቀጠና ብትደበድብም ሶስት ያነጣጠረችባቸውን ስፍራዎች ማለትም ፣ ሊማን፣ ሲቨርዶንቴስክ እና ፖፕሳናን ለመቆጣጠር እንደተሳናት የዩክሬን ጦር አስታውቋል።