በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጊኒ ወታደራዊ አመራር (ሁንታ) ሀገሪቱን ወደ ሲቪል አስተዳደር ለማሸጋገር የ39 ወራት ጊዜ አስቀመጠ


የጊኒ ወታደራዊ አገዛዝ (ሁንታ) መሪ ኮለኔል ማማዲ ዱምቦያ I ጊኒ ኮናክሪ መስከረም 2022
የጊኒ ወታደራዊ አገዛዝ (ሁንታ) መሪ ኮለኔል ማማዲ ዱምቦያ I ጊኒ ኮናክሪ መስከረም 2022

የጊኒ ወታደራዊ መንግስት አመራር የሆኑት ኮለኔል ማማዲ ዱምቦያ ፣ ሀገሪቱን ወደ ሲቨል አስተዳደር ዳግም ለመመለስ የሚረዳ የ39 ወራት የጊዜ ገደብ አስቀምጠዋል ።ትናነት ቅዳሜ በብሄራዊ ቴሌቭዥን በተላለፈ ንግግራቸው ኮለኔል ማማዲ ብሄራዊው የሽግግር ምክር ቤት ዕቀዱን ለሀገሪቱ ፓርላማ እንደሚያቀርብ ይፋ አድርጓል ።

የአሁኑ መልዕክታቸው አገዛዙ ፣ “ሁሉን አቀፍ የምክክር መወቅር “ ሲል የጠራው አካል በሚያዚያ ወር ከተመሰረተ በኃላ የተሰማ ነው።ይሄን ተከትከሎ የተጠራው ጉባኤ በርካታ ሁነኛ የፖለቲካ ቡድኖች ሳይሳተፉበት ቀርተዋል ።

በመስከረም 2021 የአውሮፓዊያኑ ዓመት በኮለኔል ማማዲ የተመራው የጊኒ ጦር ሰራዊት አመራሮች ቡድን ፣ ለሶስተኛ የፕሬዚደንትነት ዘመን የሀገሪቱን ህገ -መንግስት ለመሻሻል በጥረት ላይ የነበሩትን ሲቪል ፕሬዚደንት አልፋ ኮንዴን ከስልጣን ካስወገደ በኃላ ፣ የምዕራፍ አፍሪካ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ በምህጻሩ ኢኮዋስ በሀገሪቱ የሲቪሎች አስተዳደር ዳግም እንዲመለስ ተቀባይነት ያለው የጊዜ ገደብ እንዲቀመጥ ሲወተውት ሰንብቷል።

ማህበረሰቡ ሀገሪቱ የሽግግር እቅዷን ይፋ እንድታደርግ ፣ እስከ ባለፈው ሰኞ ድረስ የጊዜ ገደብ አስቀምጦ ነበር ። የቀድሞዋ የፈረንሳይ ቅኝ -ጊኒ ፣ ይሄን የማታደርግ ከሆነ የኢኮኖሚ እና የፋይናንስ ማዕቀብ እንደሚጠብቃትም በወቅቱ አስታውቋል ። ዘገባው የኤ ኤፍ ፒ ነው።

XS
SM
MD
LG