በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የተ.መ.ድ ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዥ ከሩሲያ ፕሬዝዳንት ጋር ተገናኙ 


ፋይል - የተ.መ.ድ ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዥ እ.አ.አ ሚያዚያ 28 2022 ከኪቭ ወጣ ብሎ የሚገኘውን ቦረዲያንካ ሲጎበኙ
ፋይል - የተ.መ.ድ ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዥ እ.አ.አ ሚያዚያ 28 2022 ከኪቭ ወጣ ብሎ የሚገኘውን ቦረዲያንካ ሲጎበኙ

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዥ ከሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ማክሰኞ እለት በሞስኮ የተገናኙ ሲሆን ከዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዚለንስኪ ጋር ደግሞ ሀሙስ እለት በኪቭ ተገናኝተው ተነጋግረዋል።

ጉተሬዥ በሞስኮ በነበራቸው ቆይታ ፑትን በደቡብ ዩክሬን በምትገኘው ማሪዮፖል ከተማ፣ በአዞቭስታል የብረት ማምረቻ አካባቢ የምታደርገውን ጥቃት አቁማ በአካባቢ ተጠልለው የሚገኙ በመቶዎች የሚቆጠሩ ንፁሃን ዜጎች ለቀው መውጣት እንዲችሉ እንደምታደርግ በመርህ ደረጃ መስማማታቸው ተገልጿል።

ሆኖም የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቩለድሚር ዚለንስኪ የሩሲያ ወታደሮች በሀራቸው በሚፈፅሙት የጭካኔ ተግባር ምክንያት የህዝብ ቁጣ እያየለ በሆደበት ወቅት ስለሰላም ውይይት ማድረግ አስቸጋሪ መሆኑን መግለፃቸውን ተከትሎ በሩሲያ እና በዩክሬን በሀከል የሚደረገውን ጦርነት ለማስቆም የሚቃሄደው ድርድር ቀጣይነት አጠራጣሪ ሆኗል። የሩሲያ ጠቅላይ ሚኒስትርም የምዕራብ ሀገራት የጣሏቸው መዕቀቦች እና የሚልኩት የጦር መሳሪያ ድርድሩን እያደናቀፈ መሆኑን ተናግረዋል።

የዩክሬን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማይን ጃፕሮቫ ረቡዕ እለት ባደረጉት ንግግር የሩሲያ ወታደሮች በሀገራቸው ላይ በርካታ የጦር ወንጀሎችን እየፈፀሙ መሆኑን በመግለፅ ተጠያቂነት እንደሚያስፈልግ አስታውቀዋል።

በቀጣይ ዋና ፀሃፊው ወደ ሴኔጋል፣ ኒጀር እና ናይጄሪያ የሚያመሩ ሲሆን በብዛት የእስልምና ሀይማኖት ያላቸው ሶስቱ ሀገራት ጉተሬዥ በየአመቱ ለረመዳን ያላቸውን ድጋፍ ለማሳየት የሚያደርጉት ጉዞ አካል መሆኑ ተገልጿል። በዚህ ጉዞአቸው ጉተሬዥ የዩክሬን ጦርነት በአፍሪካ ላይ እያሳደረ ያለውን ተፅእኖም ያጎላሉ ተብሎ ይጠበቃል።

XS
SM
MD
LG