በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ብሊንከን በሰሜን ኢትዮጵያ የሚሰጠው ርዳታ እንዲፋጠን ጠየቁ


የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አንተኒ ብሊንከን 
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አንተኒ ብሊንከን 

በኢትዮጵያ በግጭት ምክንያት በሚሊየኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በከፍተኛ የምግብ እጥረት እና የተራዘመ ረሃብ ውስጥ እንደሚገኙ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አንተኒ ብሊንከን ትላንት ባወጡት መግለጫ አስታወቁ።

በጦርነቱ የተጎዱት ማህበረሰቦች የሚያስፈልጋቸው የምግብ ርዳታ እንዲደርስ የኢትዮጵያ መንግስት እንዲሁም የትግራይና የአፋር ክልል ባለስልጣናት በቅርብ እየወሰዱት ያለው እርምጃ አበራታች ነው ያሉት ብሊንከን ሁሉም ኢትዮጵያዊ ዘላቂነት ያለውና ያልተገደበ እርዳታ እንዲያገኝ ሁሉም ወገኖች የእርዳታ አሰጣጡን ሂደት እንዲያፋጥኑና እንዲያሰፉ ጠይቀዋል። ዩናይትድ ስቴትስም ለዚህ ርዳታ መስጠቷን እንደምትቀጥል አረጋግጠዋል።

ብሊንከን አክለው ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ ግጭቱ እንዲቆም የአስቸኳይ ግዜ አዋጁን በማንሳት፣ በእስር ላይ የነበሩ ፖለቲከኞችን በመልቀቅ እና ማንኛውንም ጥቃት በማቆም መሰረት መጣላቸው አበረታች ርምጃ መሆኑን ጠቅሰው የትግራይ ሀይሎች ከአብዛኛው የአፋር አካባቢ መውጣታቸውና ግጭቱ በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ ለማድረግ ፈቃደኝነት ማሳየታቸውን አበራታተዋል። ይህን አጋጣሚ በመጠቀምም ግጭቱን ለማቆም ድርድር እንዲካሄድ እና በትግራይ መሰረታዊ አገልግሎቶች በአስቸኳይ እንዲጀመሩ መደረግ አለበት ሲሉ ለሁሉም ወገኖች ጥሪ አቅርበዋል።

XS
SM
MD
LG