በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ማሊ የፈረንሳይ የዜና ማሰራጫዎችን አገደች


ፎቶ ፋይል፦ አርኤፍአይ እና ፍራንስ 24
ፎቶ ፋይል፦ አርኤፍአይ እና ፍራንስ 24

የማሊ ወታደራዊ አገዛዝ ፍራንስ 24 ቲቪን እና ራዲዮ ፍራንስ ኢንተርናሽናልን አገደ። ይህ የሆነው የዜና ማሰራጫዎቹ የማሊ የጦር ሰራዊት በህዝብ ላይ የበደል አድራጎቶች እየፈጸመ ነው የሚሉ ሪፖርቶች ማውጣታቸውን ተከትሎ መሆኑ ታውቋል።

የአርኤፍአይ እና የፍራንስ 24 ባለቤት የሆነው ፍራንስ ሚዲያ ሞንድ የተባለው የፈረንሳይ መንግሥት ኩባኒያ የማሊ መንግሥት ያስተላለፈው የእገዳ ውሳኔ እንደደረሰው ገልጾ መሰረተ ቢስ እና በማናለብኝነት የተወሰደ ውሳኔ በማለት አውግዟል። ውሳኔውን እንዲቀለብስ የተቻለንን ሁሉ እናደርጋለን ብሏል።

አፍሪካ ነክ ጉዳዮች ላይ በብዛት የሚዘግቡት ሁለቱ ጣቢያዎች ማሊ ውስጥ ብዛት ያለው አድማጭ አላቸው።

የማሊ መንግሥት ሁለቱን ጣቢያዎች ያገዳቸው በማሊ እና የቀድሞዋ ቅኝ ገዢዋ የፈረንሳይ ግንኙነት የዚያን በዲሞክራሲ ይዞታዋ እና ሩስያውያን ቅጥር ወታደሮች አስገብታለች መባሏን ተከትሎ በከፍተኛ ደረጃ ባቆለቆለበት በአሁኑ ወቅት መሆኑ ነው።

ማሊ የፈረንሳዩን አምባሳደር ባለፈው ጥር ወር ማስወጣቷ ይታወሳል።

XS
SM
MD
LG