በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ የኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጎንደር ውስጥ በእስልምና እምነት ተከታዮች ላይ የደረሰውን ጥቃት አወገዘ


ፎቶ ፋይል፦ ጎንደር
ፎቶ ፋይል፦ ጎንደር

የኢትዮጵያ የኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጎንደር ውስጥ በእስልምና እምነት ተከታዮች ላይ የደረሰውን ጥቃት በተመለከተ አውግዞ መግለጫ አውጥቷል።

የኢትዮጵያ ኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ባለፈው ሚያዚያ 18 በጎንደር ከተማ የተፈጸመውን ግድያ፣ በቤተ እምነት ላይ ደረሰ ያለውን ቃጠሎና የሙስሊም እምነት ተከታዮችን ንብረት የማውደምና የመዝረፍ ተግባር እንደሚያወግዘው አስታወቀ።

“በየትኛውም እምነት ተከታዮቸ ዘንድ ድርጊቱ ኃጢያት፣ በፈጣሪም የሚያስጠይቅ ነው” ያለው ጉባኤው ችግሩ እንዲባባስ ሆን ብለው የሚንቀሳቀሱ አካላትም ጥፋቱን ካደረሱት የተለየ ተግባር እየፈጸሙ አለመሆናቸውን ተገንዝበው ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ ጠይቋል፡፡

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፍአለ አጥፊዎች ላይ ሕጋዊ ርምጃ እንደሚወሰድ አረጋግጠው ሆን ብለው ችግሩ እንዲስፋፋ የሚያደርጉ አካላትም ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ አሳስበዋል።

በሌላ በኩል ለቀብር በሄዱ ነዋሪዎች ላይ ዛሬም ድረስ ጥቃት መቀጠሉን አንድ የጎንደር ከተማ ነዋሪ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የኢትዮጵያ የኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጎንደር ውስጥ በእስልምና እምነት ተከታዮች ላይ የደረሰውን ጥቃት አወገዘ
please wait

No media source currently available

0:00 0:10:30 0:00

XS
SM
MD
LG