በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በቤጂንግ የኮሮናቫይረስ ምርመራ ዘመቻ ተጀመረ


የቻይና ዋና ከተማ ቤጂንግ ከሃያ አንድ ሚሊዮኑ ነዋሪዋ የሚበዛውን የሚያሳትፍ ግዙፍ የኮሮናቫይረስ ምርመራ ዘመቻ ጀምራለች።
የቻይና ዋና ከተማ ቤጂንግ ከሃያ አንድ ሚሊዮኑ ነዋሪዋ የሚበዛውን የሚያሳትፍ ግዙፍ የኮሮናቫይረስ ምርመራ ዘመቻ ጀምራለች።

የቻይና ዋና ከተማ ቤጂንግ ከሃያ አንድ ሚሊዮኑ ነዋሪዋ የሚበዛውን የሚያሳትፍ ግዙፍ የኮሮናቫይረስ ምርመራ ዘመቻ ጀምራለች። ዋና ከተማዋ ልትዘጋ ነው የሚል ስጋት አለ።

የቤጅንግ ባለሥልጣናት ትናንት ሰኞ ቁጥሩ ከማናቸውም የበዛ ህዝብ በሚኖርባት ቾያንግ ወረዳ የተጀመረውን የምርመራ ዘመቻውን ዛሬ ወደአስራ አንድ ወረዳዎች አስፋፍተውታል።

ባለፈው ሳምንት ኮሮናቫይረስ የያዛቸው አስር ታዳጊ ተማሪዎች ከተገኙ ወዲህ ዋና ከተማዋ በተጠንቀቅ ላይ ስትሆን ነዋሪዎቿ ትናንት ከተማዋ ላይ እንደሻንግሃዩ ያለ ጥብቅ የእንቅስቅቃሴ ገደብ ሊጣል ነው በሚል ሥጋት የሚያስፈልጋቸውን ለመግዛት በየገበያው ተሯሩጠዋል።

በከተማዋ የምግብ እና የሸቀጣ ሸቀጥ መደብሮች ነዋሪዎች ለረጅም ጊዜ ተሰልፈው እየጠበቁ ሩዙን አታክልቱን ወዘተ በብዛት ሲገዛ ሲሸምቱ ውለዋል። ባለስልጣናቱ አንዳንዶቹ ሰራተኞች ከቤታቸው ስራቸውን እንዲሰሩ ያሳሰቡ ሲሆን እንደ የስፖርት መስሪያ ቤቶች እና ትያትር ቤቶች የመሳሰሉትን መዝጋት ጀምረዋል።

ቤጂንግ ውስጥ ካለፈው ሳምንት ወዲህ ለኮሮና ቫይረስ መጋለጣቸው የታወቀው ሰባ ሰዎች ብቻ ሲሆኑ ሰላሳ ሶስቱ ዛሬ የተገኙ ናቸው። ትልቋ የቻይና ከተማ ሻንግሃይም በከፍተኛ ፍጥነት በሚዛመተው የኦሚክሮን ዝርያ ሳቢያ እየተስፋፋ ያለውን የቫይረሱን ስርጭት እስካሁን መቆጣጠር አልተቻላትም።

ከሃያ ስድስት ሚሊዮኑ ነዋሪዋ የሚበዛው ከቤት እንዳይወጣ የተላለፈው ጥብቅ ትዕዛዝ እንደጸና ነው። ነዋሪዎች ትኩስ ምግብ እና መድሃኒት ማግኘት አልቻልንም በማለት ቁጣቸውን እያሰሙ ናቸው።

በከተማዋ ዛሬ ብቻ ከአስር ሺህ በላይ አዲስ የቫይረሱ ተጋላጮች መገኘታቸው እና ቢያንስ ሃምሳ አንድ ሰዎች እንደሞቱ ተዘግቧል።

XS
SM
MD
LG