በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዋጋ ንረትን ለመከላከል ተመን እያወጣ መሆኑን የኦሮምያ ክልል መንግሥት አስታወቀ


የዋጋ ንረትን ለመከላከል ተመን እያወጣ መሆኑን የኦሮምያ ክልል መንግሥት አስታወቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:34 0:00

የዋጋ ንረትን ለመከላከል ተመን እያወጣ መሆኑን የኦሮምያ ክልል መንግሥት አስታወቀ

ከፋሲካና ከኢድ በዓላት ጋር በተያያዘ የሚከሰቱ ተገቢ ያልሆኑ የዋጋ ጭማሪዎችን ለመከላከል በአንዳንድ ምርቶች ላይ የዋጋ ተመን እሰከማውጣት የደረሱ እርምጃዎች እየወሰደ መሆኑን የኦሮምያ ክልላዊ መንግሥት አስታውቋል።

የዋጋ ተመኑ እንደየ አካባቢዎቹ ተጨባጭ ሁኔታ የተለያየ እንደሆነም የክልሉ ንግድ ቢሮ አመልክቷል።

በደቡብ ምዕራብ ሸዋ በምትገኘው የወሊሶ ከተማ ለምሳሌ አንድ ኪሎ ግራም የበሬ ሲጋ ከ320 እስከ 400 ብር እንዲሸጥ ተመን መውጣቱን የከተማዋ ንግድ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አስፋው ኦሉማ ለአሜሪካ ድምፅ ገልጸዋል ።

ባለፈው ሳምንት ያነጋገርናቸው ነጋዴዎች ድርቁ ለዋና ንረት አንዱ ምክኒያት መሆኑን ገልፀው የነበረ ሲሆን የኦሮምያ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ሀዋ አህመድ “ድርቅ ብቸኛው የዋጋ ንረት መንስዔ አይደለም” ብለዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያዳምጡ።

XS
SM
MD
LG