በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የመቀሌ አይደር ሪፈራል ሆስፒታል የምግብ አቅርቦት ባለመኖሩ ታካሚዎች እየመለሰ መሆኑ ተገለጸ


መቀሌ የሚገኘው አይደር ረፈራል ሆስፒታል
መቀሌ የሚገኘው አይደር ረፈራል ሆስፒታል

በጦርነት በተጎዳው የትግራይ ክልል ትልቁ ሆስፒታል ያለው የምግብ አቅርቦት ማለቁን ተከትሎ ባለፈው ሳምንት ሁለት መቶ አርባ ታካሚዎችን ወደቤታቸው እንዲመለሱ ማድረጉን ሮይተርስ ባለሥልጣናትን ጠቅሶ ዘገበ።

መቀሌ የሚገኘው አይደር ረፈራል ሆስፒታል ህሙማኑን ወደቤታቸው ለመመለስ መወሰኑ የኢትዮጵያ መንግሥት የሰብዓዊ ረድዔት መግባት እንዲችል ተኩስ አቁም ቢያውጅም ወደክልሉ በቂ ምግብ እየደረሰ አለመሆኑን የሚያስገነዝብ እንደሆነ ገልጸዋል።

ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ አንድ የአይደር ሆስፒታል ባለሥልጣን በሆስፒታሉ የቀሩት ምግብ ለራሳቸው መግዛት የሚችሉ ሦስት መቶ ስድሳ የሚሆኑ ህሙማን ብቻ መሆናቸውን እና ምግብ ወይም ገንዘብ የሌላቸውን አዲስ ህሙማን እየመለስን ነን ብለዋል። ወደቤታቸው ከሚመለሱት መካከል ማጅራት ገትር እና ቲቢ የታመሙ ህጻናት እና የኤችአይቪ ተጠቂ የሆነ ታዳጊ ያሉበት መሆኑን ሁለት ነርሶች መናገራቸውን ዘገባው ጠቅሱዋል።

የኢትዮጵያ የጤና ሚንስትር ሊያ ታደሰን እና የአደጋ መከላከል እና ዝግጁነት ኃላፊ ምትኩ ካሳን ምላሽ ለማግኘት እንዳልቻለ ሮይተርስ ገልጿል።

XS
SM
MD
LG