በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኮንጎ እና አንጎላ በሩሲያ ምትክ ለጣልያን የተፈጥሮ ጋዝ ሊያቀርቡ ነው


የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና አንጎላ ጣልያን ከሩሲያ ታገኝ የነበረውን የተፈጥሮ ጋዝ ለማቅረብ መስማማታቸው ተነገረ፡፡ የጋዝ አቅርቦቱ ጣልያን ከሩሲያ ታገኝ የነበረውን የ45 ከመቶ ድርሻ እንደሚሸፍንም የሮይተር ዘገባ አመልክቷል፡፡

የጣልያን መንግሥት ትናንት ሀሙስ ከኮንጎን ጋር በዓመት 4.5 ቢሊዮን ኩዩቢክ ሜትር ለመግዛት መፈራረሙን ተገልጿል፡፡ ከአንጎላም ጋር እንዲሁ በዓመት እስከ 1.5 ቢሊዮን ኮዩቢክ ሜትር የተፈጥሮ ጋዝ ለመግዛት ከጣልያን ጋር ባላፈው ረቡዕ መፈራረማቸው ተዘግቧል፡፡

XS
SM
MD
LG