በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባይደን ለሁለት ቀናት ጉብኝት ኦረገን ገብተዋል


ዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በፖርትላንድ ክፍለ ግዛት ኦረገን
ዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በፖርትላንድ ክፍለ ግዛት ኦረገን

ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ለሁለት ቀናት ጉብኝት በፖርትላንድ ክፍለ ግዛት ኦረገን የሚገኙት ፕሬዚዳንት ባይደን የጉብኘታቸው ትልቁ ትኩረት ያደረጉት ስላረፉበት አውሮፕላን ጣቢያ መሆኑ ተገልጿል፡፡ የፖርትላንድ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የርዕደ መሬት አደጋ ያሰጋዋል ተብሎ በተለየ ስፍራ ላይ ያረፈ በመሆኑ ይህን አደጋ ሊቋቋም የሚችል አውሮፕላን ማረፊያ ለመገንባት መታቀዱም ተመልክቷል፡፡

በፕሬዚዳንትነታቸው ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ሰሜን ምዕራብ ዩናይትድ ስቴትስ የተጓዙት ባይደን፣ ጉዳዩን ባላፈው በልግ በምክር ቤቱ እንዲጸድቅ ካደረጉት የ1 ትሪሊዮን ዶላር የመሰረተ ልማት በጀት እቅዳቸው ጋር አያይዘውታል፡፡

ውጤታማ ፖሊሲ እያራመዱ መሆኑን ለማስተዋወቅ ወደ አይዋ፣ ኖርዝ ካሮላይና፣ ኒው ሃምሸር ክፍለ ግዛቶች የተጓዙት ባይደን አሁን ካሉበት ኦረገን በኋላ ወደ ሲያትል እንደሚያቀኑ ተነግሯል፡፡

XS
SM
MD
LG