በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“ለምልመላ ሰው ይፈለጋል” መባሉን የሰሙ ኢትዮጵያውያን ሩሲያ ኤምባሲ መሰለፋቸውን ተናገሩ


“ለምልመላ ሰው ይፈለጋል” መባሉን የሰሙ ኢትዮጵያውያን ሩሲያ ኤምባሲ መሰለፋቸውን ተናገሩ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:26 0:00

“ለምልመላ ሰው ይፈለጋል” መባሉን የሰሙ ኢትዮጵያውያን ሩሲያ ኤምባሲ መሰለፋቸውን ተናገሩ

“ወጣቶች ለምልመላ ይፈለጋሉ” መባሉን የሰሙ ሰዎች አዲስ አበባ በሚገኘው የሩሲያ ኢምባሲ ፊት ለፊት ዛሬ ጭምር ተሰልፈው ነበር። አዲስ አበባ የሚገኘው የሩሲያ ኤምባሲ የወታደር ምልመላ ያካሂዳል መባሉን የሰሙ ሰዎች ወደ ኤምባሲው ሄደው መሰለፋቸውን ገልፀዋል።

በሰልፉ ላይ ያገኘነውና የቀድሞ ወታደር መሆኑን የገለፀልን አንድ ግለሰብ “የቀድሞ ወታደሮች ነን። ሥራ ማግኘት ስላልቻልን የሩሲያ ኤምባሲ ይቀጥራል ተብሎ በተነገረን መሰረት ሰነዳችንን ይዘን መጥተናል።” ብሏል።

የተባለው ምዝገባ ሊሳካ ይችላል በሚል ለሦስት ቀናት በተደጋጋሚ መመላለሱን የተናገረው ይኸው ግለሰብ፤ “አንዴ ሞላ ይሉናል። ያው እያንገላቱን ነው” ብሏል።

በሌላ በኩል በኢትዮጵያ የሩሲያ ኤምባሲ ማምሻውን ባወጣው መግለጫ ኢትዮጵያዊያን እያሳዩት እንደሆነ ስለገለፀውና ዩክሬንን በሚመለከት በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መድረኮች ላይ በቀረቡ የውሣኔ ሃሳቦች ላይ የኢትዮጵያ መንግሥት ለሩሲያ ፌዴሬሽን ሰጥቶታል ስላለው ድጋፍ ምሥጋና አቅርቦ ይሁን እንጂ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶችን በሚመለከት በወጣው በ1961ዱ የቪየና ስምምነት መሠረት የውጭ ዜጎችን ለሩሲያ የጦር ኃይሎች መመልመል የድፕሎማሲያዊ ተልዕኮው አካል አለመሆኑን አመልክቷል።

በመሆኑም በሩሲያ ጦር ኃይሎች ውስጥ ለመመልመል የሚቀርቡ ምንም ዓይነት ማመልከቻዎችን እንደማይቀበል ኤምባሲው አስታውቋል።

የዩክሬን ኤምባሲ ደግሞ በጉዳዩ ላይ መልስ መስጠት አንደማይፈልግ ለአሜሪካ ድምፅ አስታውቋል።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያዳምጡ

XS
SM
MD
LG