በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቻይና ቀጣዮቹን ጠፈርተኞች በሚቀጥለው ሰኔ ትልካለች


ፎቶ ፋይል፦ የሼንዙ - 13 የጠፈርተኞች ቡድን ዶንግፌንግ ሳይት በቻይና እአአ ሚያዚያ 16/2022
ፎቶ ፋይል፦ የሼንዙ - 13 የጠፈርተኞች ቡድን ዶንግፌንግ ሳይት በቻይና እአአ ሚያዚያ 16/2022

ቻይና በሚቀጥለው ሰኔ ተጨማሪ ሦስት ጠፈርተኞችን ወደ አዲስ የጠፈር ጣቢያ እንደምትልክ አስታውቋለች፡፡ ይህን የገለጸቸው ባላፈው ሳምንት መጨረሻ ከስድስት ወራት ቆይታ በኋላ ላይ ጠፈርተኞቿ ወደ ምድር መመለሳቸው ከተገለጸ በኋላ ነው፡፡

የቻይና የጠፈር ምርምር ፕሮግራም ባለሥልጣን የሼንዙ 14 ጠፈርተኞች ቡድን በተጀመረው የጠፈር ላይ ግንባታ ሁለት ተጨማሪ የንድፍ ግንባታዎችን ለማከናወን ለስድስት ወራት በቲያንጎንግ እንደሚቆዩ ተናግረዋል፡፡

ቻይና ለጠፈር ምርምር ትልሟን ለማሟላት የመጀመሪያውን ጠፈርተኛ ወደ ጠፈር የላከቸው እኤአ በ2003 ነው፡፡ እኤአ በ2003 ወደ ጨረቃ የሮቦት ተሽከርካሪ የላከች ሲሆን ባላፈው ዓመት ደግሞ ሌላ ተሽከርካሪ ወደ ማርስ ልካለች፡፡

ባለሥልጣናቱ ጠፈርተኞችን ወደ ጨረቃ መላክ በሚችልበት ሁኔታ እየተነጋገሩ መሆኑን ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG