በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሩሲያ ኪየቭ እና ልቪቭ ከተሞች ላይ ጥቃት አደረሰች


የዩክሬን ዋና ከተማ በቦምብ መደብደቧ ከተነገረ በኋላ ኪየቭ በሚገኝ ቻካ ውስጥ ዛሬ ቅዳሜ/ ሚያዚያ/8/ 2014 ዓ.ም የታየው ጭስ
የዩክሬን ዋና ከተማ በቦምብ መደብደቧ ከተነገረ በኋላ ኪየቭ በሚገኝ ቻካ ውስጥ ዛሬ ቅዳሜ/ ሚያዚያ/8/ 2014 ዓ.ም የታየው ጭስ

የሩሲያ የጦር አውሮፕላኖች ለቪቭ የተሰኘውን የዩክሬን ከተማ በቦምብ የደበደቡ ሆን ኪየቭ ላይም ዛሬ ሚሳይል ተኩሰዋል። ጦርነቱ በከባድ ሁኔታ እየተካሄደባት ባለውና ከፍተኛ የሰብዓዊ ቀውስ በደረሰበት ሜሪዮ ፖል ከተማ ሩሲያ ወደፊት መግፋት የቻለች ሲሆን ከተማውን መቆጣጠር ከቻለች ኪየቭን ለመያዝ ባደረገችው ውጊያ የደረሰባትን ሽንፈት የሚያካክስ ድል አድርጋ ትቆጥረዋለች ተብሏል።

ሞስኮ በዩክሬን ዋና ከተማ የሚገኝ የታንክ መጠገኛ ፋብሪካ መምታቷን ያስታወቀች ሲሆን ሜይኮሌዬቭ በተሰኘ በደቡብ ዩክሬን በኩል የሚገኝ የወታደራዊ መኪናዎች መጠገኛ ፋብሪካ ላይ እንዲሁ በተመሳሳይ የአየር ድብደባ አካሂዳለች።

የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮለድሚር ዘለንስኪ እስካሁን በጦርነቱ ከሁለት ሺህ አምስት መቶ እስከ ሶስት ሺህ የሚደርሱ የዩክሬን ወታደሮች መገደላቸውንና የሩሲያ 20 ሺህ ወታደሮች ማለቃቸውን አስታውቀዋል። ሞስኮ በመጋቢት 16፣ 1ሺህ 351 ወታደሮቿ እንደተገደሉ ካስታወቀች ወዲህ በጦርነቱ ስለደረሰው ጉዳት ከሩሲያ በኩል የወጣ መረጃ የለም።

XS
SM
MD
LG