በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ ለሚኖሩ ካሜሩናውያን ጊዜያዊ ከለላ እና የሥራ ፈቃድ ተሰጠ


ፎቶ ፋይል፦ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን
ፎቶ ፋይል፦ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን

የፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር ዩናይትድ ስቴትስ የሚኖሩ ካሜሩናውያን ከሀገር የመባረር እርምጃ እንዳይወሰድባቸው ጊዜያዊ ከለላ እና የሥራ ፈቃድ እንደሚሰጥ አስታወቀ።

ካሜሩን ውስጥ በመግሥቱ እና በታጠቁ ተገንጣዮች መካከል በቀጠለው ውጊያው ምክንያት ከዚህ ውሳኔ ላይ መደረሱን የዩናይትድ ስቴትስ የአገር ደህንነት ሚኒስቴር ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

ይህ ውሳኔ የሚመለከታቸው እስከ ትናንት እአአ ሚያዚያ 14 ቀን ድረስ ዩናይትድ ስቴትስ የገቡትን ካሜሩናውያን ሲሆን ጊዜያዊ ከለላው እና የሥራ ፈቃዱ ስራ ላይ የሚውለው ለአንድ ዓመት ከስድስት ወር የሚዘልቅ መሆኑን አመልክቷል።

በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ መሰረት በዚህ ውሳኔ ተጠቃሚ መሆን የሚችሉት ካሜሩናውያን ቁጥር ወደ አስራ ሁለት ሺህ እንደሚደርስ ይገመታል።

ፕሬዚደንት ጆ ባይደን በሀገሮቻቸው ባለ ብጥብጥ ወይም የተፈጥሮ አደጋ በመሳሰለ ልዩ ምክንያት ለመመለስ ለማይችሉ የውጭ ሀገር ሰዎች ሥራ እየሰሩ እንዲቆዩ የሚፈቅደውን የጊዚያዊ ከለላ መርኃ ግብር ጠንካራ ደጋፊ ናቸው።

የአገር ደህንነት ሚኒስትሩ አሌሃንድሮ ማዮርካስ በመግለጫቸው በሀገሪቱ ግጭት እና የቦኮ ሃራም ቡድን የሚያደርሰው ጥቃት መባባሱን ጠቅሰዋል።

XS
SM
MD
LG