በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እርዳታ የጫኑ ከባድ ተሽከርካሪዎች ወደ መቀሌ መንቀሳቀሳቸው ተገለፀ


እርዳታ የጫኑ ከባድ ተሽከርካሪዎች ወደ መቀሌ መንቀሳቀሳቸው ተገለፀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:04 0:00

እርዳታ የጫኑ ከባድ ተሽከርካሪዎች ወደ መቀሌ መንቀሳቀሳቸው ተገለፀ

እርዳታ የጫኑ ስልሳ የሚደርሱ ከባድ የጭነት ተሸከርካሪዎች ወደ ትግራይ ክልል ጉዞ ማድረግ መጀመራቸውን የኢትዮጵያ መንግሥት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።

ሚኒስትር ዲኤታ ሰላማዊት ካሳ፤ “መንግሥት የሰብዓዊ እርዳታውን ወደ ትግራይ ክልል ለማድረስ የሚጠበቅበትን ለመሥራት ዝግጁ ነው” ብለዋል፡፡

“የህወሓት ኃይሎች ከኢረብቲ ወረዳ ቢወጡም አሁንም አራት የሚደርሱ የአፋር ወረዳዎችን እንደተቆጣጠሩ ናቸው” የሚሉት የአብአላ ከተማ ከንቲባ ጣሂር ሐሰን በበኩላቸው “ኃይሎቹ ከአካባቢው ሙሉ በሙሉ ለቀው ካልወጡ በስተቀር ችግሩ መልሶ ያገረሻል” የሚል ሥጋት አሰምተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትርም ኾነ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የህወሓት ኃይሎች ከተቆጣጠሯቸው አካባቢዎች እንዲወጡ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ጫና ሊያደርግ ይገባል ሲሉ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

የትግራይ ክልል መንግሥት ከቀናት በፊት ባወጣው መግለጫው፤ “ለሰብዓዊ እርዳታ ምቹ ሁኔታ ስለተፈጠረ ለሕዝቡ በሚፈለገው መጠንና ዓይነት ሰብዓዊ እርዳታ ሊገባ ይገባል። ይህ የማይሆን ከሆነ ግን ግጭት በማስቆም ሰበብ ትግራይን በከባባና መዘጋጋት ለማቆየት አንፍቀድም።” ማለቱ ይታወሳል፡፡

/ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ/

XS
SM
MD
LG