በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአፍሪካ የቅርጫት ኳስ ሊግ አሁናዊ መረጃዎች


የደቡብ አፍሪካው ኬፕታውን ታይገርስ ቡድን የማሊ ፖሊስ ኃይል ቡድንን እጅግ ጠባብ በሆነ ውጤት 73 ለ 70 አሸንፏል
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:58 0:00

የደቡብ አፍሪካው ኬፕታውን ታይገርስ ቡድን የማሊ ፖሊስ ኃይል ቡድንን እጅግ ጠባብ በሆነ ውጤት 73 ለ 70 አሸንፏል

የአፍሪካ የቅርጫት ኳስ ሊግ የናይል ምድብ ጨዋታዎች በግብፅ ካይሮ በመከናወን ላይ ይገኛሉ። ትናንት በተደረጉ ጨዋታዎች የደቡብ ሱዳኑ ኮብራ፣ የኮንጎ ሪፐብሊኩን ቢሲ ኢስፖየር ፉካሽን 108 ለ 52 አሸንፏል።

የደቡብ አፍሪካው ኬፕታውን ታይገርስ ቡድን የማሊ ፖሊስ ኃይል ቡድንን፣ እጅግ ጠባብ በሆነ ውጤት 73 ለ 70 አሸንፏል።

በነገው ዕለት የደቡብ ሱዳን ኮብራዎች፣ ከደቡብ አፍሪካዊያን ነብሮች ጋር ይገጥማሉ፣ በከፍተኛ ጉጉት ከሚጠበቁት ጨዋታዎች መካከል አንዱ ምድቡን እየመራ የሚገኘው የአንጎላው የፔትሮ ሉዋንድ የስፖርት ክለብ በነጥብ ተበልጦ ከሚከተለው የአዘጋጇ ሀገር ግብፅ ቡድን ዛማሌክ ጋር የሚደረጉት ፍልሚያ ነው።

ነገ አመሻሽ ላይ በዶ/ር ሀሰን ሙስጠፋ የስፖርት ማዕከል ጨዋታው እከናወናል። የአሜሪካ ድምፅ የእንግሊዝኛው ክፍል ሁሉንም ጨዋታዎች በቀጥታ ያስተላልፋል።

XS
SM
MD
LG