በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ወጣቶች በዓለም አቀፍ ተቋማት ተሰሚነት ሊኖራቸው ይገባል


ወጣቶች በዓለም አቀፍ ተቋማት ተሰሚነት ሊኖራቸው ይገባል
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:50 0:00

ወጣቶች በዓለም አቀፍ ተቋማት ተሰሚነት ሊኖራቸው ይገባል

ማህሌት እንዳልኩ ስለተባበሩት መንግስታት እና ሌሎች ዓለም አቀፍ ተቋማት የማወቅ እድሉ የገጠማት ገና ልጅ እያለች ነው። በርካታ የቤተሰቦቿ አባላት በተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት በመስራታቸው፣ እሷም ትምህርቷን ስትጨርስ ተቋማቱን እንደምትቀላቀል እርግጠኛ ሆና አደገች፣ ተሳካላትም።

ማህሌት በአሁኑ ወቅት በእንግሊዝ ሀገር፣ ለንደን ውስጥ የሚገኝ ኤሴክስ ዩንቨርስቲ ውስጥ የሰብዓዊ መብቶች እና የባህል ብዝኃነት የዶክትሬት ዲግሪዋን እየተማረች ቢሆንም፣ ሁለት አመት ወደሰራችበት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኛ መርጃ ተቋም (ዩኤን ኤች ሲ አር) ተመልሳ ማገልገል፣ ትፈልጋለች። ሆኖም በተቋሙ የሚታዩ የአሰራር ችግሮችን ከመቅረፍ አንፃር ግን ተሰሚነት ይኑራት ወይም አይኑራት እርግጠኛ አይደለችም።

ከስምንት አስርት አመታት በላይ እድሜ ያስቆጠረው የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን ጨምሮ በርካታ እድሜ ጠገብ ዓለም አቀፍ ተቋማት በዓለም ዙሪያ የሰብዓዊ መብቶችን እና ሰብዓዊነትን ያማከሉ ስራዎችን ያከናውናሉ። ሆኖም ከተቋማቱ እድሜ እኩል የኖሩት ህግጋት እና ፖሊሲዎች አሁን ዓለምን ለገጠሟት ተግዳሮቶች መላ ማምጣት ባለመቻላቸው ትችቶችን ያስተናግዳሉ።

ከሰላሳ አመታት በላይ በተባበሩት መንግስታት የስደተኛ መርጃ ድርጅት ወይም ዩ ኤን ኤች ሲ አር ያገለገሉት አቶ መንገሻ ከበደ ተሰማ፣ ከሰሞኑ "" በግጭቶች እና ተቃርኖዎች ውስጥ ስኬታማ ጉዞ" በሚል ርዕስ እነዚህን ሀሳቦች ከግል ታሪካቸው እና በድርጅቱ ካሳለፉት ውጣ ውረድ ጋር አጣምረው መፅሃፍ አሳትመዋል። የመንግስታቱ ድርጅት ጠንካራና ደካማ ጎኖች ምንድናቸው ስል ጠይቄያቸዋለሁ።

አቶ መንገሻ ሰላሳ ዓመታትን በሰሩበት የስደተኛ መርጃ ተቋም ለሁለት አመት ለማገልገል እድል ያገኘችው ማህሌት በቆየችበት ግዜ በተቋሙ የታዘበችውን እንዲህ ትገልፃለች።

ይህ ብቻ አይለደም፣ የድምበር ተሻጋሪ ወረርሽኞች፣ ሽብርተኝነት፣ የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትሏቸው አደጋዎች መስፋፋት እና ሌሎች በርካታ አዳዲስ እና ነባር ችግሮችን ለመቅረፍ ዓለም አቀፍ ተቋማት ከትውልዱ ጋር መራመድ አልቻሉም ይላሉ አቶ መንገሻ።

ሜላትም በአቶ መንገሻ ሀሳብ ትስማማለች፣ ተቋማቱ ወቅታዊ የዓለም ችግሮችን መፍታት እንዲችል ተቋማቱ ለወጣቶች ድምፅ መስጠት፣ በውሳኔ መድረኮች ላይም ተሳታፊ መሆን አለበት ትላለች።

XS
SM
MD
LG