በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በጂንካ ከተማ እና አካባቢው በተፈፀመ ጥቃት 151 መኖሪያ ቤቶች መቃጠላቸው ዞኑ አስታወቀ


በጂንካ ከተማ እና አካባቢው በተፈፀመ ጥቃት 151 መኖሪያ ቤቶች መቃጠላቸው ዞኑ አስታወቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:29 0:00

በጂንካ ከተማ እና አካባቢው በተፈፀመ ጥቃት 151 መኖሪያ ቤቶች መቃጠላቸው ዞኑ አስታወቀ

በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን በጂንካ ከተማ እና አካባቢው በተፈፀመ ጥቃት አንድ መስጅድን ጨምሮ 151 መኖሪያ ቤቶች መቃጠላቸውና አንድ ሺሕ የሚደርሱ ዜጎች መፈናቀላቸውን የዞኑ የሰላም እና ፀጥታ መምሪያ አስታውቋል።

“አንፃራዊ” ያሉት ሰላም በዞኑ መስፈኑን የተናገሩት የመምሪያው ኃላፊ አቶደሞ በዛብህ በወንጅሉም የተጠረጥሩ 133 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልፀዋል።

በሌላ በኩል የጅንካ ከተማ ነዋሪዎች፤ “በወንጀሉ ተሳትፎ የሌላቸው ወጣቶች እየታፈሱ ነው” ሲሉ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአንትሮፖሎጂ መምሕርና የሕግ እና የብዛሃነት ተመራማሪ ዶ/ር ኬሬዲን ተዘራ በደቡብ ክልል የማያባራ ተመሳሳይ ጥያቄዎች እየተነሱ የፀጥታ እና የሁከት ምንጭ የሚሆኑት በሕገመንግሥቱ ክፍተት እና ፖለቲካዊ ጥያቄዎች በአግባባዊ በውይይት ይመለሳሉ የሚል ባህል እየጥፋ በመሆኑ ነው ብለዋል።

XS
SM
MD
LG