- ኦፌኮ ከታጣቂዎች ጋር ድርድር እንዲደረግ ጠይቋል
የኢትዮጵያ መንግሥት “ሸኔ” እያለ የሚጠራቸውና እራሰቸውን የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት በሚል የሚጠሩ የታጠቁ ቡድኖች ይንቀሳቀሳሉ በተባሉ ቦታዎች ያሉትን የሰላም ችግሮች ለመፍታት እየሠራ መሆኑን ክልሉ አስታወቀ።
እያከናወነ ያለው ሥራ የሕግ የበላይነት የሚያረጋግጥና የፖለቲካ ሥራዎችንም የጨመረ መሆኑን የክልሉ መንግሥት የኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛ ገልፀዋል። በኦሮምያ ክልል እንቅስቃሴ የሚያደርገው የኦሮሞ ፈዴራሊስት ኮንግረስ በበኩሉ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ፤ መንግሥት ከታጣቂዎቹ ጋር ወደ ሰላም ድርድር መግባት አለበት ሲል ጠይቋል። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ።