በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኔቶ በግዛቶቹ ድንበር ቋሚ ጦር ለማስፈር ማቀዱን - ቴሌግራፍ ጋዜጣ ዘገበ


የኔቶ አባል ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በብራስልስ ያካሄዱትን ስብሰባ ሚያዚያ 7, 2022 ሲያጠናቅቁ፣ ዋና ፀሀፊው የን ስቶትንበርግ ለሚዲያ መግለጫ ሰጥተዋል 
የኔቶ አባል ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በብራስልስ ያካሄዱትን ስብሰባ ሚያዚያ 7, 2022 ሲያጠናቅቁ፣ ዋና ፀሀፊው የን ስቶትንበርግ ለሚዲያ መግለጫ ሰጥተዋል 

ሩሲያ ወደፊት ሊኖራት የሚችለውን ጠብ ጫሪነት ለመዋጋት፣ የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃልኪዳን ድርጅት (ኔቶ) በድምበሩ ላይ ቋሚ ጦር ለማስፈር እቅድ እያወጣ መሆኑን ቴሌግራፍ የተሰኘው የእንግሊዝ ጋዜጣ፣ የኔቶን ዋና ፀሀፊ የን ስቶትንበርግን ጠቅሶ አስነብቧል።

ዋና ፀሀፊው ከጋዜጣው ጋር ባደረጉት ቆይታ፣ የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑትንን ድርጊቶች በሚያንፀባርቅ መልኩ ኔቶ መሰረታዊ ለውጦችን ለማድረግ ተዘጋጅቷል ብለዋል።

ሩሲያ በዩክሬን ላይ ያካሄደችው ወረራ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ ያልታየ ትልቁን የስደተኛ ቀውስ በአውሮፓ ያስከተለ ሲሆን የምዕራብ ሀገራት የመከላከያ ፖሊሲያቸውን በድጋሚ እያጤኑት ይገኛሉ።

XS
SM
MD
LG