በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በፈረንሳይ የመጀመሪያ ዙር ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እየተካሄደ ነው

ደቡብ ፈረንሳይ በሚገኘው ማርሴል ከተማ - ኦልጋ የተሰኘችው ውሻ ባለቤቷ ዛሬ በተጀመረው የመጀመሪያው ዙር የፕሬዝዳንት ምርጫ ድምፁን እስኪሰጥ ቆማ ትጠብቃለች 
ደቡብ ፈረንሳይ በሚገኘው ማርሴል ከተማ - ኦልጋ የተሰኘችው ውሻ ባለቤቷ ዛሬ በተጀመረው የመጀመሪያው ዙር የፕሬዝዳንት ምርጫ ድምፁን እስኪሰጥ ቆማ ትጠብቃለች 

ዛሬ በፈረንሳይ በተጀመረው የመጀመሪያ ዙር ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ፣ 48 ሚሊየን መራጮች ከ12 ተወዳዳሪዎች መሃከል የተሻለውን ለመምረጥ ድምፃቸውን ሲሰጡ ውለዋል።

ከጠዋቱ ሁለት ሰዓት የተጀመረው ምርጫ ከምሽቱ አንድ ሰዓት ላይ የተጠናቀቀ ሲሆን በአንዳንድ ትልልቅ ከተሞች እስከ ምሽቱ ሁለት ሰዓት ድረስ ቀጥሏል።

ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማርኮን ለሁለተኛ ጊዜ ለመመረጥ የሚያደርጉት ጥረት ከቀኝ አክራሪዎች ጠንካራ ፈተና ገጥሞታል። ተወዳዳሪዎች ከግማሽ በላይ ድምፅ ማግኘት ካልቻሉ ከፍተኛ ድምፅ ባገኙ የመጀመሪያ ሁለት ተወዳዳሪዎች መሀከል ሁለተኛ ዙር ምርጫ በወሩ መጨረሻ ላይ ይካሄዳል።

XS
SM
MD
LG