በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩቱብ የሩሲያን ምክር ቤት ከመድረኩ አገደ


የሩሲያው ምክር ቤት (ፎቶ ፋይል) እኤአ ሚያዝያ 7/2022
የሩሲያው ምክር ቤት (ፎቶ ፋይል) እኤአ ሚያዝያ 7/2022

ታዋቂው የቪዲዮ መድረክ ዩቱብ የሩሲያ ምክር ቤት "የዩቱብን የአገልግሎት ደንቦች ጥሷል" በሚል ዛሬ ቅዳሜ የምክር ቤቱን የመገናኛ መስመር ከመድረኩ ያገደው መሆኑን አስታውቋል፡፡

ይህ በሩሲያ ባለሥልጣናት ዘንድ ቁጣን የቀሰቀሰ ሲሆን፣ በሩሲያ በኩል "ለዩቱብ የአጸፋው ምላሽ ይሰጠዋል" ተብሏል፡፡

ንብረትነቱ የጉጉል እናት ድርጅት የአልፋ ቤት ኩባንያው የሆነው ዩቱብ፣ የተቋረጠውን አገልግሎት ወደ ሥፍራው እንዲመልስ ጉጉል ላይ ከሩሲያው ተቆጣጣሪ ባለሥልጣና ግፊት እየተደረገበት መሆኑም ተመልክቷል፡፡

የሩሲያው መገናኛ መስመሮች ቁጥጥር ኃላፊ ሮስኮማንዶዞር በሰጡት መግለጫ’ የአሜሪካ ቴክኖሎጂ ድርጅት ምዕራቡ ዓለም አገራችን ላይ የከፈተው የጸረ ሩሲያ መረጃ ጦርነት ተባባሪ ሆኗል” ሲሉ ከሰዋል፡፡

ጉጉል ስለጉዳዩ ከሮይተር ለቀረበለት ጥያቄ ምላሽ አለመስጠቱም ተዘግቧል፡፡

XS
SM
MD
LG